Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እምነትህን ጠብቅ ቁጥር 1 የተውሂድ ጠቀሜታዎች

እምነትህን ጠብቅ
ቁጥር 1
ርዕስ: ~ የተውሂድ ጠቀሜታዎች
http://www.facebook.com/emnetihintebiq
ተውሂድ ከዲን መሰረታዊ ከሆኑ ነገሮች በሙሉ ቅድሚያ ሊቸረው የቻለው አያሌ ጠቀሜታዎች ስላሉት ነው::
ከነዚህም መካከል የሚከተሉት የጎላ ጠቀሜታዎች ይገኛሉ::
1_ተውሂድ በዱንያም ሆነ በአኼራ ለሚከሰቱ ጭንቀቶችና ቅጣቶች መከላከያና መጠበቂያ ነው::
2_በልቦናው ውስጥ ቅንጣት ታክል እንኳ ተውሂድ ኖሮት ወንጀሎችን ፈፅሞ የአላህ እዝነት ሳያገኘው ቀርቶ እሳት ቢገባ ግለሰቡ እሳት ውስጥ ዘውታሪ አይሆንም:: ነገር ግን ሙሉ በሙሉ ልቦናው በተውሂድ የተሞላ ከሆነ በዱንያ ከጥመት የራቀ ይሆናል በአዀራ ደግሞ ሙሉ ደህንነትን ያገኛል (እሳት ከነጭራሹ አይገባም)::
3_ተውሂድ የአላህን ውዴታንና ምንዳውን ለማግኘት ብቸኛው ሰበብ ነው::
4_ ተውሂድን የያዘ ግለሰብ ብዙ አስከፊ ነገሮች ቢገጥሙትም እንኳ ከአላህ ውሳኔ መሆኑን በማመን በህይወቱ በጣም ደስተኛና የተረጋጋ ይሆናል::
5_ተውሂድን የያዘ ግለሰብ ለፍጠር ተገዥ ባሪያ አይሆንም::የሚፈራው:የሚከጅለው:ደጅ የሚጠናው ገታውን አንድ አላህን ብቻ ይሆናል::ይህ ነው የክብርና የልቅና መገለጫ!
6_ተውሂድን የያዘ ግለሰብ አላህ መጥፎ ከሚባል ነገር በሙሉ ሊጠብቀውና ጀነትን ሊያስገባው እንዲሁም በዚህች አለም እርሱን በማውሳት የመንፈስ እርካታን ሊያጎናፅፋቸው ቃል ገብቷል::
አላህ እርሱን በብቸኝነት ማምለክን ያጎናፅፈን ጀነቱንም ይወፍቀን!!!
# ሊንኩን_በመጫን_ፔጁን_ላይክ (like) _ያድርጉ =====>
--------------------------------
http://www.facebook.com/emnetihintebiq
--------------------------------
ኢንሻ አላህ ጠቃሚ ኢስላማዊ ዕውቀትን ይገበዩበታል!!! ሼር ማድረግ እንዳይረሡ።