Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሒድ‬ ታላቁ ቁርአን ሙፈሲር ኢማሙ ሰዐዲ (رحمه الله)


‪#‎ተውሒድ‬
ታላቁ ቁርአን ሙፈሲር ኢማሙ ሰዐዲ (رحمه الله) :–
« ምርጥ ዕውቀት ማለት የተውሒድ ዕውቀት ነው»
[ተይሲር ገፅ 125]
ሐማድ አልአንሳሪ (رحمه الله) :–
« ቁርአን በተውሒድ ጀምሮ በተውሒድ ያበቃል ። አላህ በተውሒድ ኖራቹ በተውሒድ ሙቱ ያለን ይመስላል»
[ ተፍሲር አልፋቲሃ ገፅ 54]
ኢማም ኢብን አቢ አልኢዝ (رحمه الله):–
« ቁርአን ሙሉው ስለተውሒድ ነው »
[ሸርሕ አልአቂደቱ ጠሀዊያ (1)]
ኢብኑል ቀዪም (رحمه اله):–
« የአንድ ሰው ተወኩል (በአላህ ላይ መመካት)
ሙሉ አይሆንም ተውሒዱ ሙሉ እስካልሆነ ድረስ ። በመሆኑም የተወኩል እውነታ ልብ ውስጥ ያለው ተውሒድ ነው»
በሌላ ቦታም
« የተውሒድ ሙሉዕነት የሚኖረው ልብ ውስጥ ከአላህ ሌላ ምንም ሳይኖር ነው»
[መዳሪጁ ሳሊኪን ፣ተወኩል (1/526) (3/485)]
ኢማም ኢብን ረጀብ (رحمه الله):–
« ተውሒድን ለማረጋገጥ ዛሬውኑ ጣር ። በርግጥም አላህን (ውዴታ) በዚህ መንገድ እንጂ መድረስ አትችልም ። የተውሒድን መብት ለመትከል ጉጉ ሁን ። ምክንያቱም ከአላህ ቅጣት የምትድነው በሱ እንጂ በሌላ አይደለምና»
[ከሊማ አልኢኽላስ ገፅ 54]
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (رحمه الله):–
« ከተውሒድና ከኢኽላስ የበለጠ ለልብ ጠቃሚ ነገር የለም»
በሌላ ቦታም
« የተውሒድ ምስክርነትን መስጠት የመልካምን እና ከወንጀል መመለስ (የንስሀን) በር ይከፍታል ። የእኩይን በር ደግሞ ይዘጋል»
[መጅሙዑ ፈታዋ (10/625) ፣ (10/256)]