Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጠለዐል በድሩ ዐለይና ሚን ሳኒየተል ወዳዕ ..... በጥሞና ይነበብ


ዜማው ይህን ይመስላል
ጠለዐል በድሩ ዐለይና ሚን ሳኒየተል ወዳዕ
طلع البدر علينا من ثنيات الوداع
ወጀበ ሹክሩ ዐለይና ወዳዓ ሊላሂ ዳዕ
وجب الشكر علينا ما دعا لله داع
ይሄ ዜማ የተወሰደው ቀጥሎ ከተጠቀሰው ሐዲስ ነው
لما قدم النبي صلى الله عليه وسلم المدينة جعل النساء والصبيان والولائد يقولون
طلع البدر علينا وجب الشكر علينا
أيها المبعوث فينا من ثنيات الوداع
ما دعا لله داع جئت بالأمر المطاع))
___________________
ሆኖም ይሄ ሲራ የቀረበበት ሐዲስ ከፅሁፍም ከሠነድም አንፃር መሰረት አልባ መሆኑን ምን ያህሎቻችን እናውቅ ይሁን ?
እሺ ተከተሉኝማ
በታላቁ የሐዲስ ሊቅ የሆኑት ኢማም ሃፊዝ ኢብኑ ሃጀር አል አስቀላኒ (ረሒመሁላህ) መሰረት ይሄ ሐዲስ የተወሳው በአቡ ሰዒድ በሸረፈል ሙስጠፋ እና በአልኻሊ በአል ፈዋዒድ በብዙ ዘጋቢዎች ሰንሰለት በዑበይዱላህ ቢን አዒሻ ዘጋቢነት ይህ ክስተት ተዘግቧል ። [ፈትሑልባሪ 7/326]
በተመሳሳይ አል ኢማም በይሐቂ (ረሒመሁላህ) በደላዒል አልኑቡዋ [2/506-7] ዘግበውታል [አል ቢዳያ ወኒሃያ 2/202 ሲልሲለቱለድ ዶዒፋህ 2/63]
ነገር ግን ዘጋቢው ዑበይዱላህ ቢን አዒሻ ታሪኩን ስናጠና አስረኛ ደረጃ ላይ ያለ ዘጋቢ ሆኖ እናገኘዋለን ። ይህም ማለት ታዕቢዮችን ያላገኘ ዘጋቢ ያደርገዋል ። (ታዕቢይ ፡ ሰሃቦችን ያገኘ)
ይህ ዘጋቢ በ 228 ዓ.ሒ የሞተ ሲሆን በአማካይ ብንወስድ እንኳን በርሱና በሒጅራ ሰዎች መካከል በትንሹ የ120 ዐመታት ሰፊ ልዩነት መኖሩን እንገነዘባለን ። ለዚህም በርሱና በሒጅራ ሰዎች መካከል የተቆረጡ (ያልተገለፁ) ብዙ ዘጋቢ ግለሰቦች ክፍተትን ያሳየናል።
1) ኢማም ሃፊዝ ኢብኑ ሐጀር አስቀላኒ (ረሒመሁላህ) ይህን ሃዲስ ‹‹.. ሙዕደል ሰንሰለቱ ችግር ያለበት..›› ብለው ብይን ሰጥተውበታል ። [ፈትሑልባሪ7/327]
2) የኢማም ሃጀር አስተማሪ የሆኑት ሃፊዝ አል ኢራቂ (ረሒመሁላህ) የቢን አዒሻ ዘገባ ሙዕደል ደካማ እና ለማስረጃነት ሊቆም የማይችል ብልውታል [አል መዋሂብ አል ለዱኒያህ 1/313]
3) ኢማም ናስሩዲን አል አልባኒ (ረሒመሁላህ) [በሲልሲለቱ አድ-ዶዒፋህ 2/63] ላይ ሐዲሱ ሙዕደል መሆኑን እና ሶስት ወይንም ከዚያ የበለጡ ዘጋቢዎች የተቆረጡና ያልተጠቀሱ መሆናቸውን ፅፈዋል ።
4) ዶክተር አክረም ዲያ ዑመሪ :- ‹‹.. ጠለዐል በድሩ ዐለይና ስለሚለው ሐዲስ ደግሞ ሰንሰለቱ የተቆረጠ ደካማ ሐዲስ ነው..›› ብለዋል [አስ ሲራህ አንነበዊያህ አስ ሰሒሓ 1/219]
5)ዶክተረ አኒስ ቢን አሕመድ አል ኢንዶኖዚ [.. ሐበር ወነሺድ በሚለው ኪታብ 43] ላይ ስለዚህ ሐዲስ ሲናገሩ ‹‹.. ከብዙ ምርምር በኋላ ማወቅ እንደቻልነው ይህ ሐዲስ የዘገበው የዜማው ሁነት እና የቀረበበት የፅሁፍ ይዘት ደካማና እንግዳ የሆነ ነው››
6) አሽሸይኽ ሙሃመድ ሃሳን ሙሃመድ በዚህ ሐዲስ ዙሪያ ጠለቅ ያለ ጥናትያደረጉ ሲሆን ይህ ሐዲስ በመሰረቱ የቀረበበት አገላለፅ በወቅቱ መዲና ላይ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች የንግግር ዘይቤ ሳይሆን ሊሆን የሚችለው ከሒጅራበኋላ የነበሩ የሶስተኛው ክፍለ ዘመን ሰዎች አገላለፅ ሲሆን በግጥሙ መሃከል የሚገኘውን (ሸረፈተል መዲና) የሚለው ቃልንም እንዴት የመዲና ሰዎች ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም መዲናን ሊያልቋት እንደመጡ ሊያውቁ ቻሉ ? በሚል ይበልጥ የሐዲሱ ጥቅል አገላለፅንም ጥያቄ ውስጥ ያስገቡታል ። [ዲራሰቱንሐዲሲየቱን አልኸበር ወነሺድ 12-13]
ይህ እንዲህ ከሆነና የአላህ መልዕክተኛ ቅበላ እንዲህ እንዳልነበር ከተረዳን ታዲያ እንዴት ነበር የሚል ጥያቄን ያስነሳል ።
እነሆ...
የረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የመዲና ቅበላ..
በራዕ ቢን አዚብ (አባቱም እሱም ባልደረባ የነበሩ ወጣት ልጅ) እንዲህ አለ :-
‹‹ አቡ በክር ሲዲቅ ረዲየላሁ ዐንሁ ወደ አባቴ አባቴ መጣና ኮርቻ ከገዛ በኋላ ለአባቴ አዚብ እንዲህ አለው.. ‹ልጅህ ወደ ቤት ይህን ይዞልኝ ይምጣ ከዚያም አባቴ እኔን ተሸክመህ ይዘህለት ሂድ ብሎ አዘዘኝ እኔም የታዘዝኩትን አደረግኩ አባቴም ከአቡ በክር ሲዲቅ ጋር ገንዘቡን ለመቀበል ተከትሎ መጣ ለአቡ በክርም እንዲህ አለው ‘‘ያ አቡ በክር ሆይ ዋጋውን ከረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ጋር ስለነበራቹ ጉዞ አድርግልኝ ’’
አቡ በክር ረዲየላሁ አንሁም ስለነበረው ጉዞ ሰፋ ያለ መረጃ ሰጠው እንዲህም ብሎ.. ‹‹ እኛ መዲና የደረስነው በምሽቱ ጊዜ ሲሆን መዲና የነበሩ ሰዎች የአላህ መልዕክተኛ ማን ጋር ሊያርፉ እንደሚችሉ ይነጋገሩ ነበር ። ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለምም እንዲህ አሉ እኔ ከነጃር ጎሳዎች ጋር አርፋለው ፤ የዐብዱል ሙጠሊብ ዘመዶች እንግዳቸው እሆናለው ››
አቡ በክር እንዲህ ሲል ቀጠለ .. ‹‹ ወንዶችና ሴቶች ወደ ግንብ እየዘለሉ ወጡ ልጆችና አገልጋዮች መንገዱ ላይ ተበተኑ ፤ እናም እንዲህ እያሉ ይጣሩ ነበር
‹ ሙሀመድ የአላህ መልዕክተኛ! ሙሀመድ የአላህ መልዕክተኛ! ›
[ ሙስሊም ]
ኢማም ሐኪም እንዲህ ይላሉ .. ‹‹ .. ሰዎች ፣ ልጆች እና አገልጋዮች እንዲህ እያሉ ተጣሩ.. ‹ ሙሀመድ መጣ የአላህ መልዕክተኛ መጣ አላሁ አክበር ሙሀመድ መጣ የአላህ መልዕክተኛ መጣ ከዚያም ሲነጋ ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ወደጠየቁት ቦታ ሄደው አረፉ..›› [ ቡኻሪና ሙስሊም]
ከነዚህ ሐዲሶች መረዳት እንደምንችለው ረሱል ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የተደረገላቸው ቅበላ አንዳንድ የሲራ መፅሃፍት እንደሚዘግቡት ያልተጣራና ደካማ የዜማና የድቤ ቅበላ ሳይሆን የመዲና ሰዎች የአላህ መልዕክተኛን መልዕክተኛ መሆናቸውን በመመስከር በክብር እንደተቀበሏቸው ያሳያል ።
በአሁን ጊዜ በሚያሳዝን ሁኔታ ይሄን ደካማ የዜማና የድቤ ቅበላ በመመርኮዝ አንዳድንዶች ሙዚቃ ፣ ነሺዳ ፣ ድቤና ሌሎች የሙዚቃ መሳሪያዎች ለመፈቀዳቸው ማስረጃነት ሲያቀርቡት ይስተዋላል ። አልፎ ተርፎም ይሄን ነሺዳ (ጠለዐል በድሩ) አንዳንድ ሕፃናት በነሺዳ በየመድረሳው ሲያፍዙት ይስተዋላል ። ከዚያም ብሶ በነሺዳ መልክ በሙዚቃ መሳሪያ ታጅቦ ይሄን ነሺዳ በሲዲ ሲያባዙት ቻናሎች ላይ ሲያቀርቡት ይታያል ። ይህ መታረም ያለበት ትልቅ ስሕተት መሆኑን ሳንጠቁም አናልፍም ።
[[ إِنَّ فِي ذَٰلِكَ لَذِكْرَىٰ لِمَن كَانَ لَهُ قَلْبٌ أَوْ أَلْقَى السَّمْعَ وَهُوَ شَهِيدٌ ﴿٣٧﴾]]
በዚህ ውሰጥ ለእርሱ ልብ ላለው ወይም እርሱ (በልቡ) የተጣደ ኾኖ (ወደሚነበብለት) ጆሮውን ለጣለ ሰው ግሳጼ አለበት፡፡ {ሱረቱ ቃፍ-37}



AS

Post a Comment

0 Comments