Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ታሪካዊ ውይይት

“ቁርአን ፍጡር ነው!” የሚለውን የአላህን የመናገር ባህሪ የሚያፈርስ የክህደት አቋም ባለመቀበላቸው ታስረው የነበሩ አንድ በእድሜ ጠና ያሉ አሊም ከአህመድ ኢብን አቢ ዱአድ(1) ጋር ኸሊፍው አል―ዋሲቅ(232 ዓ.ሂ የሞተ) ባለበት ያደረጉትን ምልልስ በአጭሩ እንደሚከተለው አቀርበዋለሁ፦

― [ኸሊፍው ለዓሊሙ፦]  “ከአህመድ ኢብን አቢ ዱአድ ጋር ተወያዩ!”… 
― [ዓሊሙ፦] “አሚሩ´ል―ሙእሚኒን ሆይ! የምንመላለሳቸውን ቃላት በደንብ ብታስተውልልን..?”
― [ኸሊፍው፦] “ እሺ!”
― [ዓሊሙ ለኢብኑ አቢ ዱአድ፦] “ይህ ሰዎችን ወደ እርሱ የምትጣራው (የቢድዓህ) ንግግርህ የዲን እምነት ውስጥ የሚካተት ግዴታና ያለ እርሱ ዲን የማይሞላ ነውን? ”
― [ኢብኑ አቢ ዱአድ፦] “አዎን!”
―[ዓሊሙ፦] “አላህ መልክተኛውን(ሰለላሁ አለይሒ ወሰለም)ወደ ባሮቹ ሲልክ እርሳቸው እንዲያስተላልፉት ከታዘዙት የዲን ጉዳይ የሸሸጉት ነገር አለ? ”
― [ኢብኑ አቢ ዱአድ፦] “የለም”! 
―[ዓሊሙ፦] “ታዲያ መልክተኛው ወደዚህ ንግግርህ ተጣርተዋል?! ”
― [ኢብኑ አቢ ዱአድ፦] (ፀጥ!) (1) 
― [ዓሊሙ፦] “ተናገር እንጂ!”
― [ኢብኑ አቢ ዱአድ፦] (አሁንም ፀጥ!)
― [ዓሊሙ ለኸሊፋው ] “አሚሩል´ሙእሚኒን ሆይ አንድ(ብለህ ቁጠርልኝ)!”
― [ኸሊፋው፦] “አንድ!”
― [ዓሊሙ ለኢብኑ አቢ ዳኡድ፦] “ ማነው እውነተኛው? ሀይማኖታችንን እንዳሟላልን የነገረን {አል―ማኢዳህ 3} አላህ? ወይስ ይህንን መጤ ንግግርህን እስከምናምን ድረስ ጎዶሎ እንደሆነ የነገርከን  አንተ?! ”
― [ኢብነ አቢ ዱአድ፦] (ፀጥ!)
― [ዓሊሙ፦] “መልስልኝ!”
― [ኢብኑ አቢ ዱአድ፦] (አሁንም ፀጥ!) 
―[ዓሊሙ ለኸሊፋው] “አሚረ´ል ሙእሚኒን ሆይ!  ሁለት በልልኝ! ”
― [ኸሊፋው፦] “ሁለት!”
― [አሊሙ ለኢብኑ አቢ ዱአድ፦] “እስቲ ንገረኝ! ይህንን ንግግርህን መልክተኛው አውቀውት ነበር ወይስ አላወቁትም? ”
― [ኢብኑ አቢ ዱአድ፦] “አውቀውታል! ”
― [ዓሊሙ፦] “ሰዎችን ወደዚያ ጠርተዋል? ”
― [ኢብኑ አቢ ዱአድ፥] (አሁንም ፀጥ!) 
― [ዓሊሙ ለኸሊፋው፦] “አሚሩ´ል ሙእሚኒን ሆይ! ሶስት በልልኝ! ”
―[ኸሊፋው፦] “ሶስት!”
― [ዓሊሙ ለኢብኑ አቢ ዱአድ፦] “እንደምትለው የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይህንን እያወቁት ተከታዮቻቸውን ወደዚህ ባለመጥራታቸው ተብቃቅተዋል? ”
― [ኢብኑ አቢ ዱአድ፦] “አዎን! ”
― [አሊሙ፦] “አቡ በክር፥ ዑመር፥ ዑስማንና ዐሊይም እንደዚሁ በዝምታ ተብቃቅተው ነበር? ”
― [ኢብኑ አቢ ዱአድ፦] “አዎን!”
― [አሊሙ ወደ ኸሊፋው በመዞር፦] “ረሱልን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አቡ በክርን፥ ዑመርን፥ዑስማንን ዐሊይን ያብቃቃቸው ዝምታ የማያብቃቃህ ከሆነ፦ ለነሱ የተመቻቸው የማይመቸው ሁሉ አላህ ምቾትን ይንሳው!”

― [ኸሊፋው፦]“አዎን! ረሱልን አቡ በክርን፥ ዑመርን፥ዑስማንንና ዐሊይን ያብቃቃቸው ዝምታ የሚያብቃቃን ከሆነ፦ለነሱ የተመቻቸው የማይመቸው አላህ ምቾትን ይንሳው!! ” 

ከዚህ ጊዜ ጀምሮ ኸሊፋው የግል አቋሙን እንዳስተካከለ ይነገራል! (1) 
____________________________________

(1) ይህ የጀህሚይ―ያህ አቀንቃኝ አል―ኢማሙ አህመድን ለማስገደል ሲጥር የነበረ የሱን―ናህ ቀንደኛ ጠላት ነው! 

(1) “አዎን!” ካለ በምንም መረጃ ሊደግፈው የማይችል አይን ያፈጠጠ ቅጥፈት ስለሚሆን ነው ዝም ያለው! መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ወደ ተዕጢል ተጣርተዋል ብሎ የሚሞግት ካለ የምላሱን ቅጥፈት ልቦናው ያውቀዋል! 

(1) “አሸ―ሸሪያህ” ሊ´ል―ኣጁር―ሪይ ገፅ 91፣ “ታሪኹ በግዳዲ” ሊ´ል―ኸጢብ (11/271)፣ “አል―ኢባናህ ” ሊ ´ብኒ በጥ―ጣህ (2/269)፣ እና ሌሎች መዛግብት ላይ ሰፍሯል።
________________________________
ምንጭ፦ የአማኞች ጋሻ ከሚለው የኡስታዝ ኤልያስ አህመድ (ከገፅ 223 እስከ 226) መፅሐፍ የተወሰደ።

Post a Comment

0 Comments