Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሒጃብ

ሒጃብ
ኢስላም ያለገደብ ወንድና ሴት እንዲቀላቀሉ፣ አንዱ የሌላውን ስሜት በመቀስቀስ እንዲፎካከሩና ልቅ የአለባበስ ስርዐት እንዲከተሉ መፍቀድ የሚያስከትለው ችግር በግለሰብ ላይ ብቻ የሚገደብ ሳይሆን መላው ማህበረሰብ የሚያዳርስ መሆኑን ያስተምራል። ጉዳቱም ከባድና ችላ ሊባል የማይችል መሆኑንም ያስገነዝባል።
ኢስላም ከትዳር በፊት በማንኛውም ስሜት ቀስቀሽ እና ለወሲብ የሚገፋፋ ድርጊት ይቃወማል። ነገር ግን ተግባሩን በተጋቡ ጥንዶች መካከል ግን ያበረታታል።
ለማመልከት ነው» ይላሉ። ይህ ከእውነታው ጋር ምንም ግንኙነት የሌለው እሳቤ ነው። በኢስላም ሒጃብ የለበሰች (ሰውነቷን በሚገባ የሸነፈች) ሴት በህብረተሰቡ ዘንድ ክብር ይሰጣታል። ስርዐት ባለው አለባበሷም ከወንድ ልጅ ስሜት ማራገፊያነት ትድናለች። ኢስላማዊ አለባበስ የምትለብስ ሴት ለህብረተሰቡ የምታስተላልፈው መልዕክት «በእኔነቴ ልታከብሩኝ ይገባል፤ እኔ የሥሜታችሁ ማራገፊያ ቁስ አይደለሁም» የሚል ነው።
ሴትን ልጅ ለወንድ ደስታ ብሎ የስሜት ማራገፊያ ማድረግ ነፃነትና እኩልነት አይደለም፡፡ እንኪያስ በኢስላም የተከለከለ ኢ-ሰብአዊ ተግባር ነው። የሙስሊም ሴት ነፃነት የሚገለፀው በውጫዊ ቅርጿ ሳይሆን በውስጣዊ ማንነቷ ስትለካ ነው።
ሁሌም ሌላውን ለማስደሰት ለመልካቸው፣ ለቅርፃቸውና ለወጣትነታቸው እንዲጨነቁ የተገደዱት የምዕራቡ አለም ”ነፃ” ሴቶች በባርነት ወጥመድ ውስጥ የተጠመዱ ናቸው። ሁሌም ስለሚመለከቷቸው እንጂ ስለ ህይወታቸው የማያስቡ አገልጋዮች።
አንዳንድ ሴቶች ፊታቸውን እና መዳፋቸውን ጭምር መሸፈንን ይመርጣሉ። ይህ አለባበስ ሴሰኛ ከሆኑ ወንዶች ሴቶችን የሚያቅብ መሳሪያ ሲሆን በአላህ መልዕክተኛ(ሰ.ዐ.ወ) የተደነገገ ሸሪዐ ነው። ይህን ኢስላመዊ ስርዐት መቀበል ብሎም መተግበር አላህን መታዘዝ ሲሆን ማመፅና ብሎም መቃወም ደግሞ ከኢስላም የሚያስወጣ ክህደት ነው።
ሴቶች በኢስላም
አላህ ዘንድ ሰዎች እኩል ናቸው።
«ከናንተ በላጫችሁ ይበልጥ አላህን ፈሪያችሁ ነው» ይለናል አላህ። አላህ አንዳችንን ካንዳችን የሚያስበልጠው በስራ እንጂ በማንነት አይደለም። እናም ፍትሀዊው ጌታ ወንዱንም ሴቱንም እንደሰራው ስራ በመጪው አለም ይመነዳል።
ኢስላም ሴትን ከጃሂሊያ ግድያ አውጥቶ ለክብር አብቅቷታል። ሴት የመኖር የማግባት ቤተሰብ የማፍራት መብቶች ባለቤቶ አድርጐታል። ሴት ልጅ የመማር የማወቅና ዲኗን የመረዳት መብት አላት። የማንም መጫወቻ ያለመሆን የመከበርና የመታፈር መብትም አላት። ስሟም ያለአግባብ እንዳይጎድፍ ኢስላም ዘብ ቆሞላታል።
ትዳር በኢስላም የሚበረታታ ህጋዊ ጥምረት ነው። ኢስላም ያገባችም ሆነች ያለገባች ሴት የግል መብቷ እንዲጠበቅ ያዛል። ንብረቷ እነዳይነካና ወጪዋን ባሏ እንዲሸፍን ያስገድዳል። ስትጋባም ሆነ ስትፋታ ሀብቷን ለማንም አታካፍልም የማንንም አትካፈልም። በኢስላም ሴት ልጅ ለባሏ ክብር ሲባል የአባቷን ስም አትቀይርም። ባሏም የሸሪዓን መስፈርት የማያሟላ ከሆነ ፍቺ የመጠየቅ መብቷም የተከበረ ነው። ሴት ልጅ የመውረስ የማውረስ የመውለድ እንዲሁም በልጆቿ ከባሏ ሶስት እጥፍ የመቀረብ መብትም አላት። እናት ናትና።
ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በተናገሯቸው ብዙ ሀዲሶች ወንዶች በሴቶች ላይ ድንበር እንዳያልፉ አበክረው አስጠንቅቀዋል። ሴቶችንም በዲናቸው እንዲጠነክሩ ግዴታዎቻቸውን እንዲወጡም ተጣርተዋል። ጥሪያቸውን ማድመጥ ብሎም መተግበር የኛ ሀላፊነት ነው!!!

Post a Comment

0 Comments