Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥቂት መውሊድን የተመለከቱ ፈትዋዎች

""ጥቂት መውሊድን የተመለከቱ ፈትዋዎች""
بسم الله الرحمن الرحيم
فتاوى العلماء في حكم الإحتفال بمولد سيد الأنبياء
باللغة الأمهرية ترجمه: أحمد بن آدم الشراري
መውሊድን ማክበር በተመለከተ ታላላቅ የሱና ዑለሞች የሰጧቸው ፈትዋዎች
1ኛ የሸይኽ ሙሐመድ ኢብኑ ኢብራሂም ፈትዋ
-የቀድሞ የሳዉዲ ዓረቢያ ሙፍቲ- "ረሒመሁሏህ"
የነቢዩን ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ልደት ማክበር ደጋግ ቀደምቶች ዘንድ የታወቀና ከዲንም የሚቆጠር አልነበረም:: ምርጥ ትውልድ መሆናቸውን ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የመሰከሩላቸው ደጋግ ቀደምቶች (ሰሓባዎችን፣ ታቢዒዮችና ተከታዮቻቸው) ዘንድ መውሊድ አለመታወቁና እሱንም አለማክበራቸው መጤና አዲስ ፈጠራ መሆኑን እናውቃለን::
2ኛ የኢብኑ ባዝ ፈትዋ "ረሒመሁሏህ"
የነቢዩንም ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ይሁን የሌላ የማንኛውንም ሰው ልደት ማክበር በሸሪዓ አይፈቀድም:: ምክንያቱም ይህ በዲናችን መሰረት ከሌላቸውና አዲስ ከተፈጠሩ ነገሮች ነው ለምን ቢባል፥ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም፣ አራቱ ቅን ተተኪ መሪዎቻቸውና ከነሱ ውጪም ያሉ ሰሓቦች እንዲሁም የነሱ ተከታይ የነበሩ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የመሰከሩላቸው መልካም ሶስት ክፍለ ዘመናት ውስጥ የተገኙ ደጋግ ቀደምትም መውሊድን አላከበሩም::
3ኛ የኢቡኑ ዑሠይሚን ፈትዋ "ረሒመሁሏህ"
በመጀመሪያ ደረጃ፥ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የተወለዱበት ዕለት በእርግጠኝነት አይታወቅም:: በመሆኑም ረቢዕ-አል አወል 12ኛውን ዕለት ማክበር ከታሪክ አንጻርም መሰረት የለውም
ሁለተኛው፥ ከሸሪዓ አንጻርም መውሊድን ማክበር ቢድዓና ሐራም ነው:: ቡኻሪይ እና ሙስሊም በዘገቡት ሐዲስ ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ብለዋል፥
( من أحدث في أمرنا هذا ما ليس منه فهو رد )
" በዲናችን አዲስና መሰረት የሌለውን ነገር የፈጠረ ሰው ስራው ተመላሽ ነው (ተቀባይነት የለውም) ብለዋል::
4ኛ የሸይኽ ፈውዛን ፈትዋ "ሐፊዘሁሏህ ወሸፋህ"
ዘመን-ወለድ ቢድዓዎች ብዙ ናቸው ይህም የዚህች ምድር ህይወት ማብቂያ በመዳረሱና ትክክለኛው የሸሪዓ ዕውቀት በመቀነሱ እንዲሁም ወደ አዳዲስ የዲን ላይ ፈጠራዎችና ከኢስላም ጋር ወደ ሚጻረሩ ነገሮች የሚጣሩ ሰዎች በመብዛታቸው ምክንያት ነው:: ከዚህም አንዱ፥ ከክርስትና እምነት ተከታዮች ጋር የሚያመሳስል የሆነው የነቢዩን ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ልደት የማክበር ፈጠራ ነው ይህን ዕለት የማክበሩ ህደትም ከሺርክ፣ የተለያዩ ከሸሪዓ ጋር ከሚጋጩ ተግባራት፣ ነቢዩን ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በተመለከተ ድንበር ከማለፍ ወዘተ አይጠራም::
5ኛ የፈትዋ ቋሚ ኮሚቴ ምላሽ
የነቢዩን ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ልደት ማክበር በዲኑ ላይ አዲስ ከተፈጠሩ ነገሮች መካከል አንዱ ነው:: ነቢዩም ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም የሚከተለውን ማለታቸው ይታወቃል፥ " በዲናችን አዲስና መሰረት የሌለውን ነገር የፈጠረ ሰው ስራው ተመላሽ ነው (ተቀባይነት የለውም)"