Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተወሡል

ተወሡል
☞ ትርጉም ፦ ተወሡል ሁለት ትርጉም አለው
1 በእምነት እና በመልካም ስራ ወደ አላህ መቃረብ ማለት ይህን አስመሎክቶ አላህ እንዲህ ይላል
(( ﻳَﺎ ﺃَﻳُّﻬَﺎ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﺁﻣَﻨُﻮﺍْ ﺍﺗَّﻘُﻮﺍْ ﺍﻟﻠّﻪَ ﻭَﺍﺑْﺘَﻐُﻮﺍْ ﺇِﻟَﻴﻪِ ﺍﻟْﻮَﺳِﻴﻠَﺔَ ﻭَﺟَﺎﻫِﺪُﻭﺍْ ﻓِﻲ ﺳَﺒِﻴﻠِﻪِ ﻟَﻌَﻠَّﻜُﻢْ ﺗُﻔْﻠِﺤُﻮﻥ ))
" እናንተ ያመናቹሁ ሆይ አላህን ፍሩ ወደ እርሡም መቃረብን ፈልጉ ትድኑም ዘንዳ በርሡ ሠንገድ. ላይ ታገሉ "
☞ ኢብኑ ጀሪር (ወደ እርሱ መቃረብን ፈልጉ) የሚለውን ወደአላህ እርሡ በሚወደው መልካም ስራ ወደ እርሱ
መቃረብ ሢል ይተረጉመዋል
በሌላ አንቀፅ እንደዚህ ይላል
"ﺃُﻭﻟَﺌِﻚَ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺪْﻋُﻮﻥَ ﻳَﺒْﺘَﻐُﻮﻥَ ﺇِﻟَﻰ ﺭَﺑِّﻬِﻢُ ﺍﻟْﻮَﺳِﻴﻠَﺔَ ﺃَﻳُّﻬُﻢْ ﺃَﻗْﺮَﺏُ ﻭَﻳَﺮْﺟُﻮﻥَ ﺭَﺣْﻤَﺘَﻪُ ﻭَﻳَﺨَﺎﻓُﻮﻥَ ﻋَﺬَﺍﺑَﻪُ ﺇِﻥَّ ﻋَﺬَﺍﺏَ ﺭَﺑِّﻚَ ﻛَﺎﻥَ ﻣَﺤْﺬُﻭﺭًﺍ "
"እነዚያ እነርሡ የሚገዟቸው ምንም ያክል ወደ ጌታቸው የቀረቡ ቢሆኑም ወደ ጌታቸው የሚያቃርባቸውን ስራ ይፈልጋሉ እዝነቱንም ይከጅላሉ ቅጣቱንም ይፈራሉ የጌታህ ቅጣት የሚፈራ ነውና "
☞ በአንቀፁ ላይ እንደተመለከትነው ከአላህ ውጫ ሦሊህ ፣ ነብይ፣ መላኢካ… ናቸው እየተባሉ የሚለመኑ አካላቶች ምንም ያክል ወደ አላህ የቀረቡ እናንተ አላህ ዘንድ ከየትኛውም ፍጥረት በላይ የሚወደዱ ቢሆኑም መልካም ስራዎችን የተከለከሉ እናንተ መጥፎ ነገራቶችን እየራቁ ወደ አላህ መቃረብን እንደሚፈልጉ ነው
2. ሁለተኛው የተወሡል ትርጓሜ ፦ በጀነት ውስጥ ያለች ከፍተኛ ደረጃ ነች ከአላህ ባርያዎች መካከል ለአንዱ የአላህ ባርያ ብቻ ነው የምትገባው ረሡል ሠለላሁ. አለይሒ ወሠለም እንዲህ ይላሉ
"ﺇﺫﺍ ﺳﻤﻌﺘﻢ ﺍﻟﻤﺆﺫﻥ ﻓﻘﻮﻟﻮﺍ ﻣﺜﻞ ﻣﺎ ﻳﻘﻮﻝ ﺛﻢ ﺻﻠﻮﺍ
ﻋﻠﻲ ﻓﺈﻧﻪ ﻣﻦ ﺻﻠﻰ ﻋﻠﻲ ﺻﻼﺓ ﺻﻠﻰ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻠﻴﻪ ﺑﻬﺎ ﻋﺸﺮﺍ ﺛﻢ ﺳﻠﻮﺍ ﺍﻟﻠﻪ ﻟﻲ ﺍﻟﻮﺳﻴﻠﺔ ﻓﺈﻧﻬﺎ ﻣﻨﺰﻟﺔ ﻓﻲ ﺍﻟﺠﻨﺔ ﻻ ﺗﻨﺒﻐﻲ ﺇﻻ ﻟﻌﺒﺪ ﻣﻦ ﻋﺒﺎﺩ ﺍﻟﻠﻪ ﻭﺃﺭﺟﻮ ﺃن ﺃﻛﻮﻥ ﺃﻧﺎ ﻫﻮ ﻓﻤﻦ ﺳﺄﻝ ﻟﻲﺍﻟﻮﺳﻴﻠﺔ
ﺣﻠﺖ له ﺍﻟﺸﻔﺎﻋﺔ" ﺻﺤﻴﺢ ﻣﺴﻠﻢ
" አዛን ባዩን በሠማችሁት ግዜ የሚለውን በሉ ከዛም በኔ ላይ ሠለዋት አውርዱ እነሆ በኔ ላይ አንድ ሠለዋት ያወረደ በሡ ላይ አላህ አስር ሠለዋት ያወርዳል ከዛም ለኔ ወሢላ የተባለችውን ጠይቁልኝ እሧ በጀነት ውስጥ ያለች ደረጃ ነች ከአላህ ባርያዎች መካከል ለአንዱ እንጂ ለሌላ አትገባም ያ አንዱ ሠው እኔ እንድሆን እፈልጋለው ወሢላን የጠየቀልኝ ሰው የኔ ምልጃ ለሡ ይረጋገጥለታል "ሙስሊም
★የተወሡል አይነታዎች
☞ ተወሡል ጥቅሉ ለሁለት ይከፈላል እነሡም የሚፈቀድ እና የማይፈቀድ
✔ የሚፈቀደው የተወሡል አይነት ቁርአን እና ሀዲስ ወደ አላህ እንደሚያቃርብ ማመላከቻ የሠጡት ነገር በአጠቃላይ ወደ አላህ ያቃርባል የሚፈቀደው የተወሡል አይነትም ውስጥ ይካተታል ከሚፈቀዱ የተወሡል አይነታዎች መካከል
★ በአላህ መልካም ስሞች ወደ አላህ መቃረብ አላህ እንዲህ ይላል
"ﻭَﻟِﻠّﻪِ ﺍﻷَﺳْﻤَﺎﺀ ﺍﻟْﺤُﺴْﻨَﻰ ﻓَﺎﺩْﻋُﻮﻩُ ﺑِﻬَﺎ ﻭَﺫَﺭُﻭﺍْ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ
ﻳُﻠْﺤِﺪُﻭﻥَ ﻓِﻲ ﺃَﺳْﻤَﺂﺋِﻪِ ﺳَﻴُﺠْﺰَﻭْﻥَ ﻣَﺎ ﻛَﺎﻧُﻮﺍْ ﻳَﻌْﻤَﻠُﻮﻥَ "
" ለአላህ መልካም ስሞች አሉት በሡም ለምኑት እነዚያን በስሙ የሚዘባርቁትን ተዋቸው ይሠሩት በነበረው ይመነዳሉ "
☞በአላህ ስሞች ስንቃረብ በሁለት አይነት መልኩ ሊሆን ይችላል
1 ጥቅል አድርገነው (የአላህን ስሞች በአጠቃላይ በአንድ ቃል በመጥራት) ልክ ነብዩ ለላሁ አለይሒ ወሠለም በዱአቸው ላይ ያደርጉት እንደነበረው
"…ﺃﺳﺄﻟﻚ ﺑﻜﻞ ﺍﺳﻢ ﻫﻮ ﻟﻚ ﺳﻤﻴﺖ ﺑﻪ ﻧﻔﺴﻚ ﺃﻭ ﻋﻠﻤﺘﻪ ﺃﺣﺪﺍ ﻣﻦ ﺧﻠﻘﻚ …"
"…ለአንተ በሆኑ ስሞችህ እጠይቅሀለው እራስህን የጠራህባቸው ወይም ከፍጡራንህ ለአንዱ ባሣወቅከው …"
2 የአላህን ስሞች በነጠላ እየጠራ ከሚጠይቀው ነገር ጋር ግንኙነት ያላቸውን የአላህ ስሞች በመጥቀስ ወደ አላህ እየተቃረበ አላህን መለመን ምሣሌ ምህረት የፈለገ መሀሪ ከሚለው የአላህ ስም ጋር እያገናኘ ይለምናል አላህ እንዲህ ይላል
(ﻭﺗﺐ ﻋﻠﻴﻨﺎ ﺇﻧﻚ ﺃﻧﺖ ﺍﻟﺘﻮﺍﺏ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ)
"ማረን አንተ መሀሪና አዛኝ ነህና "
✔ ሙሉ በሆኑ በአላህ ባህሪያቶች መቃረብ ይህንንም ለሁለት ከፍለን መመልከት እንችላለን
1 ጥቅል ባህሪውን በአንድ ቃል በመጥራት
"ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺇﻧﻲ ﺃﺳﺄﻟﻚ ﺑﺄﺳﻤﺎﺋﻚ ﺍﻟﺤﺴﻨﻰ ﻭﺻﻔﺎﺗﻚ ﺍﻟﻌﻠﻰ "
"አላህ ሆይ መልካም በሆኑ ስምችህ እናንተ የተላቁ በሆኑ ባህሪያቶችህ እማፀንሀለው "
2 ከምንጠይቀው ነገር ጋር ተያያዥነት ካላቸው የአላህ ባህሪ ጋር በማያያዝ
"ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺑﻌﻠﻤﻚ ﺍﻟﻐﻴﺐ ﻭﻗﺪﺭﺗﻚ ﻋﻠﻰ ﺍﻟﺨﻠﻖ ﺃﺣﻴﻨﻲ ﻣﺎ ﻋﻠﻤﺖ ﺍﻟﺤﻴﺎﺓ ﺧﻴﺮﺍ ﻟﻲ ﻭﺗﻮﻓﻨﻲ ﺇﺫﺍ ﻛﺎﻧﺖ ﺍﻟﻮﻓﺎﺓ ﺧﻴﺮﺍ ﻟﻲ …"
"አላህ ሆይ የገይብ ነገር በማወቅህ በፍጡራን ላይ ባለህ ሀይል ይሁንብህ በህይወት መኖሬ ለኔ ጥሩ ከሆነ አንተ ታውቃለህ በህይወት አኑረኝ መሞቴ ለኔ ጥሩ ከሆነ ግደለኝ… "
✔ በአላህ እናንተ በመልዕክተኛው በማመኑ ወደ አላህ መቃረብ
"ﺭَﺑَّﻨَﺎ ﺁﻣَﻨَّﺎ ﺑِﻤَﺎ ﺃَﻧﺰَﻟَﺖْ ﻭَﺍﺗَّﺒَﻌْﻨَﺎ ﺍﻟﺮَّﺳُﻮﻝَ ﻓَﺎﻛْﺘُﺒْﻨَﺎ ﻣَﻊَ ﺍﻟﺸَّﺎﻫِﺪِﻳﻦ"َ
"ጌታችን ሆይ አንተ ባወረድከው አመንን መልዕክተኛውንም ተከተልን ከሹሀዳዎች ጋር ፃፈን. "
✔ቀደም ብለን በሠራነው መልካም ስራ ወደ አላህ መቃረብ
☞ ይህ ለመብቃቱ እንደ መረጃ የሚሆነን እረዘም ስለሚል እና ብዙዎቻችን ዘንድ የሚታወቅ ስለሆነ መጥቀስ አላስፈለገም እንደ ማስታወሻ ግን
☞ ሦስቱ ሠዎች መሽቶባቸው ወደ አን ዋሻ ገብተው ዋሻውን ቋጥኝ ዘጋባቸው ከዛም ቀደም ብለው የሠሯቸውን መልካም ስራዎች እያስጠጉ አላህን ተማፀኑት ከቋጥኙ ስር መውጣት ቻሉ።
✔ደካማነትን በማመን እንዲሁም በመናገር ወደ አላህ መቃረብ
ﻓَﺴَﻘَﻰ ﻟَﻬُﻤَﺎ ﺛُﻢَّ ﺗَﻮَﻟَّﻰ ﺇِﻟَﻰ ﺍﻟﻈِّﻞِّ ﻓَﻘَﺎﻝَ ﺭَﺏِّ ﺇِﻧِّﻲ ﻟِﻤَﺎ ﺃَﻧﺰَﻟْﺖَ ﺇِﻟَﻲَّ ﻣِﻦْ ﺧَﻴْﺮٍ ﻓَﻘِﻴﺮ
ٌ
"(ሙሣ) ለሁለቱ ካጠጣላቸው ቡሀላ ወደ ጥላው ዘወር አለና ወደ እኔ ከምታወርደው ከመልካም ነገር ፈላጊ ነኝ "
✔ የሠራውን ወንጀል በማመን ወደ አላህ እየተቃረቡ አላህን መማፀን
"ﻗَﺎﻻَ ﺭَﺑَّﻨَﺎ ﻇَﻠَﻤْﻨَﺎ ﺃَﻧﻔُﺴَﻨَﺎ ﻭَﺇِﻥ ﻟَّﻢْ ﺗَﻐْﻔِﺮْ ﻟَﻨَﺎ ﻭَﺗَﺮْﺣَﻤْﻨَﺎ ﻟَﻨَﻜُﻮﻧَﻦَّ ﻣِﻦَ ﺍﻟْﺨَﺎﺳِﺮِﻳﻦَ "
"ጌታችን ሆይ ነፍሦቻችንን በድለናል ካልማርከን እና ካላዘንክል ከከሰሩት እንሆናለን አሉ "
✔ በህይወት ያሉ መልካም ሠዎችን ዱአ እንዲያደርጉልን በመጠየቅ ወደ አላህ መቃረብ
"ﻗَﺎﻟُﻮﺍْ ﻳَﺎ ﺃَﺑَﺎﻧَﺎ ﺍﺳْﺘَﻐْﻔِﺮْ ﻟَﻨَﺎ ﺫُﻧُﻮﺑَﻨَﺎ ﺇِﻧَّﺎ ﻛُﻨَّﺎ ﺧَﺎﻃِﺌِﻴﻦَ"
"አባታችን ሆይ ለወንጀላችን ምህረትን ጠይቅልን እኛ ስህተተኞች ነን "አሉ
☞ ከላይ የተጠቀሡት በአጠቃላይ የሚፈቀዱ እናንተ የሚበቁ የተወሡል አይነታዎች ናቸው
2 የማይፈቀደው የተወሡል አይነት ፦ ይህ የተወሡል (የመቃረቢያ) አይነት ቁርአን ሀዲስ እንዲሁም የሠለፎች ንግግር ማመላከቻ ያልሠጠበት ተግባር ወይም ንግግር ነው
☞ ይህ የተወሡል አይነት ለሁለት ይከፈላል እነሡም ሽርክ የሆነው እናንተ ቢድአ የሆነው
1 ሽርክ የሆነው የተወሡል አይነት ፦ይህ የተወሡል አይነት ከእስልምና ያስወጣል ምክንያቱም የኢባዳ አይነታዎችን ከአላህ ውጪ አሣልፎ መስጠት ስለሚስተዋልበት. ተወሡል ነው በሚል ሠበብ ወደ ሦሊህ ሠዎች ቀብር በመሔድ አልያም ባሉበት ሆነው ሦሊህ ናቸው ብለው. ሚያስቧቸው ሠዎች የአላህ መብት የሆኑትን ኢባዳዎች አሣልፈው ይሠጧቸዋል ምሣሌ ዱአን የይድረሡልኝ ጥሪን እና ሌሎችንም የኢባዳ አይነቶች አሣልፈው ይሠጧቸዋል ይህ ተግባር የሚከናወነው በተወሡል ሽፋን ነው. ያም ሆነ ይህ ተወሡል የሚል ሽፋን ስለ ተሠጠው ሽርክ ከመሆን አያግደውም ተወሡልንም በተሣሣተ መልኩ መረዳታቸው ነው እዚህ ሽርክ ውስጥ የጣላቸው. የሚያሣዝነው እና የሚያስፈራው ነገር ግን የተወሡል ሽፋን ተደርጎላቸው የሚለመኑት አካላቶች. ይህን ጥሪ ወይም ልመና አለመስማታቸው ነው አላህ እንዲህ ይላል
"ﻭَﻣَﻦْ ﺃَﺿَﻞُّ ﻣِﻤَّﻦ ﻳَﺪْﻋُﻮ ﻣِﻦ ﺩُﻭﻥِ ﺍﻟﻠَّﻪِ ﻣَﻦ ﻻ ﻳَﺴْﺘَﺠِﻴﺐُ ﻟَﻪُ ﺇِﻟَﻰ ﻳَﻮﻡِ ﺍﻟْﻘِﻴَﺎﻣَﺔِ ﻭَﻫُﻢْ ﻋَﻦ ﺩُﻋَﺎﺋِﻬِﻢْ ﻏَﺎﻓِﻠُﻮﻥَ "
"ከአላህ ውጪ ያለን ቢጠራው እስከ ቂያማ. ቀን ድረስ ምላሽ የማይሠጠውን አካል ከሚለምን ሠው ይበልጥ ጠማማ የለም የሚለመኑት አካላት ከመለመናቸው ዝንጉዎች ናቸው "
☞ ይባስ ብለው የቂያማ ቀን ዛሬ የለመናቸው ላይ ጠላት ይሆናሉ አላህ እንዲህ ይላል.
"ﻭَﺇِﺫَﺍ ﺣُﺸِﺮَ ﺍﻟﻨَّﺎﺱُ ﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﻟَﻬُﻢْ ﺃَﻋْﺪَﺍﺀ ﻭَﻛَﺎﻧُﻮﺍ ﺑِﻌِﺒَﺎﺩَﺗِﻬِﻢْ ﻛَﺎﻓِﺮِﻳﻦ"
"ሠዎች ሢቀሠቀሡ ለእነሡ ጠላታቸው ይሆናሉ እነሡን በማምለካቸውም ይክዳሉ "
☞ ይህ ሁሉ ሢሆን ግን አላህ ሡብሀነሁ ወተአላ ዛቻ አዘል በሆነ ቃል እሡን እንድንለምነው ያዘናል
"ﻭَﻗَﺎﻝَ ﺭَﺑُّﻜُﻢُ ﺍﺩْﻋُﻮﻧِﻲ ﺃَﺳْﺘَﺠِﺐْ ﻟَﻜُﻢْ ﺇِﻥَّ ﺍﻟَّﺬِﻳﻦَ ﻳَﺴْﺘَﻜْﺒِﺮُﻭﻥَ ﻋَﻦْ ﻋِﺒَﺎﺩَﺗِﻲ ﺳَﻴَﺪْﺧُﻠُﻮﻥَ ﺟَﻬَﻨَّﻢَ ﺩَﺍﺧِﺮِﻳﻦَ "
"ጌታችሁ ለምኑኝ አለ እነዚያ እኔን ከመለመን የሚኮሩ ጀሀነምን የተዋረዱ. ሢሆኑ ይገቧታል "
☞ ይህ የተወሡል አይነት ሽርክ ነው ከኢስላም ያስወጣል
2 ቢድአ የሆነ የተወሡል አይነት ፦ ይሄ የተወሡል አይነት ከኢስላም ባያስወጣም ከባድ ወንጀል ከመሆኑም ባለፈ ወደ ሽርክ ለመድረስ መንገድ ይሆናል ለምሣሌ
"ሦሊህ በሆነው ባርያህ. ይሁንብህ ይሄን ስጠኝ "
"በነብዩ ይሁንብህ " በነብዩ ክብር. ይሁንብህ "እና ይህን የመሣሠሉ መረጃ ያልመጣላቸው ንግግሮች በመጠቀም የሚሠራ የተወሡል አይነት ነው
አላህ በሡ ከማጋራት ይጠብቀን!!!

Post a Comment

0 Comments