Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

"ሰለፍ" የሚለውን ቃል አል አላመቱ አል ሙሃዲስ አል ሸህ .....

Dawud Yassin
"ሰለፍ" የሚለውን ቃል አል አላመቱ አል ሙሃዲስ አል ሸህ መሃመድ ነስረዲን አል አልባኒ ሲያብራሩ "ሰለፍ" የሚለው ቃል በቋንቋም በሸሪዓም የታወቀ ነው ነብያችን (ሰዐወ) ለህልፈት ሰበብ በሆናቸው በሽታ ላይ እያሉ ለልጃቸው ፋጢማ እንዲህ ይሏት ነበር
فا تقی الله وصبری ونعم السلف أنا لک
"አላህን ፍሪ ትግስትም አድርጊ እኔ ላንቺ ያማረ ተቀዳሚ ነኝ"
በመቀጠልም ራሱን ወደሰለፍ አላስጠጋም የምል ሰው ይላሉ እኔ ሙስሊም አይደለሁም እንደማለት ነው ንግ ግሩ የሚያሲዘው ምክንያቱም የትክክለኛ ሙስሊም መግለጫ "ሰለፉነ ሳሊህ "ናቸው ከነርሱም የመ ጀመሪያው ነብያችን( ሰዐወ) ናቸው ነብያችን (ሰዐወ )እንዲህ ብለዋል "
خیر الناس قرنی ثم الذین یلونهم ثم الذین یلونهم
"ሰለፊ "ተብሎ መጠራት የተጀመረው ትናንትና እንደሆነ አድርገው የሚያስቡ" የፊክራ" ብዥታ የመታቸው ሰዎች አሉ እውነታው ግን በተቃራኒው ነው
በጀግንነቱ የምንምሰክርለት ታላቁ ዓሊም ሸይህ አል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ እንዲህ ይላሉ
لا عیب علی من" أظهر مذهب السلف وانتسب إلیه واعتزی إلیه بل یجب قبول ذلک منه بالإتفاق فإن مذهب السلف "لا یکون إلا حقا
"የሰለፎችን አካሄድ ግልፅ ያደረገና ራሱን ወደ ነርሱ ያስጠጋ የሆነ ሰው ምንም ነውር የለበትም እንደሁም ከርሱ መቀበሉ ግድ መሆኑ ሁሉም ተስማምተውበታል ምክንያቱም የሰለፎች መንገድ ከእውነት ውጪ አይሆንምና..."
ኢማሙ አል ዘሃቢ የቀደምት ዓሊሞችን ታሪክ ሲተረጉም እከሌ "ሰለፊ "ነበር ይላል
ለምሳሌ የአቢ ጣሂርን የኢብኑ ሰላህን የዳረ ቁጥኒን የሙሃመድ ቢን ሙሃመድ ቢን አል ፈድል አል በህራኒን የየህያ ቢን ኢስሃቅ ቢን ኸሊል አል ሸይባኒ ለሁሉም" ሰልፊ" ነበሩ ሲል ያስቀምጣል
በዘመናችን ስላሉ "ሰለፊ" ዓሊሞቻችን ደግሞ ብጠቅስ መዝለቂያም የለኝም
ግን በአላህ ይሁንብን እውነቱን ለማን ብለን ነው የምንረግጣት ?እነዚህ ዓሊሞች ሁሉ የአንድነት ፀር ናቸው ማለት ነው?
አላህን ፈርተን ተውበት እናድርግ!

Post a Comment

0 Comments