ምስጋና ለአለማት ጌታ ለአላህ የተገባ ነው። የሰውልጅን ፈጥሮ በከንቱ ላልተወው። እንዳውም በመልዕክተኛው ከጨለማ ላወጣው። የአላህ ሰላምና ውዳሴ በነብዩ ፣ በቤተሰቦቻቸውና በጓዶቻቸው ላይ ሁሉ ይስፈን። እያንዳንዱ ሙስሊም ሊያውቀው ከሚገባ ቁም ነገር ዋነኛው የተፈጠረበት አላማ ነው። አላህ ለምን እንደፈጠረን ሲገልፅ በቁርዐኑ
«ጋኔንንም ይሁን ሰውን ሊያመልኩኝ እንጂ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም።» (ዛሪያት 56) ይላል።
አላህ ሰዎችን ፈጥሮ አልተወም። በል በየጊዜው መልዕክተኞችን እየላከ ወደ ተፈጠሩበት አላህን በብቸኝነት ማምለክ (ተውሂድ) ይጠራ ነበር። ከባዕድ አምልኮ(ሽርክም) ያስጠነቅቅ ነበር። ከመጀመሪያው መልዕክተኛ ኑህ(ዐለይሂ.ሰላም) እስከ ነብያት መደምደሚያ ነቢዩ ሙሐመድ (ሰለለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሁሉም ነቢያት አንግበው የተላኩት ተውሂድና ተውሂድ ነበር።
«በየህዝቡም ሁሉ ዉስጥ አላህን አምልኩ ጣዖታትንም ራቁ በማለት መልዕክተኞችን በእርግጥ ልከናል» (ነህል 36)
ነቢዩም (ሰለለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)ወደ ተውሂድ ለ23 አመታት ተጣሩ። በተለይም ደግሞ በመጀመሪያዎቹ የነብይነት 10 አመታት በብቸኝነት ተውሂድን ሰበኩ። አላህ ብቻ ተነጥሎ እንዲመለክ ጣሩ፤ በመካ ግፍና በደሉ ሲያይልም ወደ መዲና ተሰደዱ። በዚያም ተውሂድንና ሌሎች የእስልምና ድንጋጌዎችን አስተማሩ። እነዚያ በላጭ ትውልዶች(ሰለፎች) የነቢዩን ፈለግ በመከተል ይህንን ዳዕዋ በአለም አሰራጩ። አምልኮት ለአላህ ብቻ ሆነች። ኢስላምም በተውሂድ የበላይ ሆነ።
ነቢዩ ሶሀቦቻቸውን ለዳዕዋ ሲልኩ የሚያስጨብጧቸው ተልዕኮ ቅድሚያ ተውሂድ ነበር።
ኢብኑ አባስ እንዳወሩት
ኢብኑ አባስ እንዳወሩት
ነቢዩ(ሰለለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ሙዐዝን ወደ የመን በላኩት ግዜ እንዲህ አሉት «አንተ የምትሄድባቸው ሰዎች የመጽሀፍ ባለቤቶች ናቸው። መጀመሪያ የምትጠራቸው ወደ “ላኢላሀ ኢለላህ”(ከአላህ ውጪ በእውነት የሚገዙት አምላክ እንደሌለ) ይሁን። ይህን ከተቀበሉክ አላህ አምስት ወቅት ሶላት ግዴታ እንዳደረገባቸው አሳውቃቸው……» (ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል)
ከተውሂድ ቅድሚያ የሚሰጠው አንድም አንገብጋቢ ጉዳይ የለም። ምክንያቱም የአንድ ሰው እስልምና መሰረቱ ተውሂድ ስለሆነ። ተውሂዱ የተስተካከለ መላ ስራው ይስተካከላል። መሰረቱ ከተበላሸ ግን ግንቡ ያምራል ተብሎ አይጠበቅም። የሰራውም ስራ ከሽርኽ ከተነካካ ዋጋ የለውም።
“ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፡፡ በእርግጥም ከከሓዲዎቹ ትኾናለህ ማለት ወደ አንተም ወደ እነዚያም ካንተ በፊት ወደ ነበሩት በእርግጥ ተወርዷል” (ዙመር-65)
አላህ በሱረቱ አንዐም የ18 ነብያትን ስም ጠቅሶ
“ባጋሩም ኖሮ ይሠሩት የነበረው ከነሱ በታበሰ ነበር፡፡” ይላል።
አቂዳውን(እምነቱን) ጠንቅቆ ማወቅ በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ዋጂብ ነው። ራስን ከተለያዩ መሰረተ ቢስ እምነቶች ማጥራት ቅሮት የሌለው ጉዳይ ነው። ብሎም በእውቀትና በሂክማ ሌሎችን ማስተማር ለድርድር የማይቀርብ ሀላፊነት ነው።አላህ እንዲህ ይላል-

“እነሆ ከአላህ ሌላ አምላክ አለመኖሩንም ዕወቅ፡፡ ስለ ስህተትህም ለምእመናንም ምሕረትን ለምን፡፡“ (ሙሀመድ:19)
ይሁንና ብዙዎች እጅግ ተዘናግተዋል። ተውሂድን ከመማር ርቀዋል፤ መሰረቱን ጥለው በቅርንጫፋዊ ጉዳዮች ባተሌ ሁነዋል። የሚያሳዝነው ዳዒዎችና ዕውቀትን ፈላጊዎች ለተውሂድ ትኩረት ነፍገዋል፤ ከመማርና ማስተማር ታቅበዋል፣ ይባስ ብለው ከሽርክ ከማስጠንቀቅ ዝምታን መርጠዋል እናም እስልምናን የሚሞግቱ ሰዎች ዳግም ወደ ሽርክ ነጉደዋል። ነቢዩ (ሰለለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) የተመቱበትን፣ የተወጉበትን፣ የተሰቃዩበትን ተውሂድ አሽቀንጥረው ጥለው ያ ነቢያችን ወደ ነቀፉት፣ ወዳወገዙት፣ ብሎም ወደ ተዋጉት ፀያፍ ተግባር ተሰማርተዋል። ወሊዮችንና አሊሞችን ማክበር በሚል ሽፋን ድንበር አልፈዋል ብሎም ቀብር አምልኮ ውስጥ ተዘፍቀዋል። ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን።
«አላህ በርሱ የማጋራትን(ወንጀል) አይምርም፡፡ ከዚህም ወዲያ ያለውን ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው (ከእውነት) የራቀን መሳሳት በእርግጥ ተሳሳተ፡፡» (ኒሳእ-116)
አንተ ሙስሊም ሆይ! ቁርዐንን ባነበብክ ወቅት አብዛኛውን አናቅፁን በአቂዳ ዛቢያ ሲዞር ታገኘዋለህ። አቂዳን በማስተካከል ላይ ትኩረት ሲሰጥ ታያለህ። እናም ቁርዐን ትኩረት ለሰጠው ጉዳይ ትኩረት ልትሰጥ ይገባሀል! ለራስህ፣ ለቤተሰብህና ለኡማው አሳቢ ከሆንክ፤ ነቢዩ (ሰለለላሁ ዓለይሂ ወሰለም) ለተላኩለት፣ ለለፉለት፣ ለደሙለት መልዕክት ቅድሚያ መስጠት ይኖርብሀል!
አዎን! በርግጥ የሙስሊሞች ሁኔታ የሚያስጨንቅህ እንደሆን ነቢዩ ለቆሙለት ቁም፤ ለለፉለት ድከም፤ በፋናቸው ተጓዝ፤ አንተንም ዙሪያህንም ከጥፋት ታደግ ግን እውቀትን አስቀድም። ራስህን በትክክለኛው አቂዳ(እምነት) ገንባው። ጎንበስ በልና ቅራ፤ ቀና በልና አስተጋባው!
“በል «ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም»” (ዩሱፍ 108)

ለማንኛውም ነገር እውቀት ይቀደማልና ወደ አቂዳ ትምህርት ተሽቀዳደም። ይህን አንገብጋቢ አና ወሳኝ ርዕስ ከመማር አንዳችም ነገር ሊገድብህ አይገባም። ተውሂድ መሰረት ነው። መማር፣ ማወቅ፣ መረዳት ግድ ይላል። ያለመሰረት ዲን አይገነባምና ዛሬ ነገ ሳትል እምነትህ እወቅ።ከቂርዐት ሀለቃዎች ተሳተፍ። ጊዜህን ተጠቀምበት!
አዩሀል ሙስሊም! ነስር በሜዳ አይገኝምና ታገል፤ ትግልህ አቂዳን በማስተካከል ሲጀምር ውጤቱ ያማረ ይሆናል፤ አሊያ ግን ልፋታችን ሁሉ የእምቧይ ካብ ይሆናል። ተውሂድን ተማር፣ አስተምር ታገስ። አላህ ካንተ ጋር ነውና!!!
አዩሀል ሙስሊም! ነስር በሜዳ አይገኝምና ታገል፤ ትግልህ አቂዳን በማስተካከል ሲጀምር ውጤቱ ያማረ ይሆናል፤ አሊያ ግን ልፋታችን ሁሉ የእምቧይ ካብ ይሆናል። ተውሂድን ተማር፣ አስተምር ታገስ። አላህ ካንተ ጋር ነውና!!!
وَالَّذِينَ جَاهَدُوا فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا وَإِنَّ اللَّهَ لَمَعَ الْمُحْسِنِينَ ﴿العنكبوت: ٦٩﴾
«እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው፡፡» አንከቡት-69