Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ተውሂድን ማስተማር ሽርክን ማስጠንቀቅ ተሳዳቢ አያስብልም፡፡

ተውሂድን ማስተማር ሽርክን ማስጠንቀቅ ተሳዳቢ አያስብልም፡፡
ነብየላህ ኢሳን (አለይሂ ሰላም) አታምልኩ፤ አላህን ብቻ አምልኩ፤ ማለት ኢሳ ተሰደበ ማለት ነውን??? አይደለም፡፡ እንዲያውም ፍትሃዊነት ነው፡፡
ሱናን ማስተማር ቢድዐን እና ባለቤቶቹን ማስጠንቀቅ ተሳዳቢ አያስብልም፡፡
የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ፈለግ ብቻ እንከተል፤ ቢድዐን ከነባለቤቶቻቸው እንራቅ፤ አዳዲስ መጤ መንገዶችን በጠቅላላ እንራቅ ማለት ተሳዳቢ አያስብልም፡፡
ለምሳሌ፡- ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ስለ መጤ የቢድዐ ቡድኖች ለምሳሌ ‹‹ጀበርያ›› ተናግረዋል፡፡ አብደላህ ኢብን ኡመር (ረድየላሁ አንሁም) ስለ መጤ የጥመት ቡድን ‹‹ቀደርያ›› ጠንከር አድርገው ተናግረዋል፡፡
ልክ እንደዚሁ ሁሉ ታላላቅ አኢማዎቻችን ሰሃባዎችን አናስነካም ብለው ‹‹ከራፊዳዎች›› ለሰሃባዎች ጥብቅና ቆመው ነበር፡፡ ይህም ተሳዳቢ አላስባላቸውም፡፡
ልክ እንደዚሁ ነብያት በተጣሩበት የተጣራ፤ የሰሀባዎችን ፈለግ የተከተለ፤ ሰሃባዎችን ያከበረ እና እነሱን የሚነኩትን ሰዎችም ይሁን ጠበቆቻቸውን በማስረጃ መልስ የሰጠ ተሳዳቢ አይደለም፡፡
ሃቅን በባጢል መሸፈን ከቶውንም አይቻልም፡፡