Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በጁምዓ የማለዳ ፈጅር ሰላትን በጀመዓ መስገድ


በጁምዓ የማለዳ ፈጅር ሰላትን በጀመዓ መስገድ አንድ ሰው በሳምንቱ ውስጥ ከሚሰግዳቸው ሰላቶች በሙሉ በላጭ ነው!
ሹዓቡል ኢማን በተሰኘው ኪተሰባቸው ላይ አል ኢማም አልበይሀቂይ ከኢብኑ ኡመር እንዳስተላለፉት፤ የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል «አላህ ዘንድ ከሰላቶች ሁሉ ብልጫ ያለው በጁምአ እለት የሱብሂን ሰላት በጀመዓ መስገድ ነው» አልባኒ ሰሂሁል ጃሚእ (1119) ላይ ሰሂህ ብለውታል።
ሀዲሱን እንደ አልሀፊዝ ኢብኑ ረጀብ እና አል ሀፊዝ ኢብኑ ሀጀርና ሌሎችም ኡለማዎች በኢብኑ ኡመር ንግግርነት የተላለፈውን ዘገባ ትክክለኝነት በመጠቆም (መውቁፍ) ነው ብለዋል። ይሁንና፤ ኢብኑ ኡመር ከመልእክተኛው ያገኙት እርግጠኛ ትምህርት ሳይኖር
በዚህ መልኩ ከአላህ የሚገኝን ምንዳ ያትታሉ የሚለው የማይታሰብ ነውና፤ ይህን ንግግሩን ወደ መልእክተኛው በመጠጋት የ (መርፉዕ) ሁክምና ደረጃ ማሰጠቱ አያጠራጥርም።

አላህ ይህንን ምንዳ ይወፍቀን!
صلاة الفجر جماعةً يوم الجمعة خير صلاة يصليها المسلم في أسبوعه
عن ابن عمر قال : قال الرسول صلى الله عليه وسلم : ( أفضل الصلوات عند الله صلاة الصبح يوم الجمعة في جماعة ) . رواه البيهقي في "شعب الإيمان" . وصححه الألباني في صحيح الجامع (1119)

Salah Ahmed