Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰላት ያለ ጡሃራ እና ዉዱ፤ ኢባዳ ያለ ኢኽላስ እና ሱና....

ሰላት ያለ ጡሃራ እና ዉዱ፤ ኢባዳ ያለ ኢኽላስ እና ሱና....
መስጂዶች ረመዳን ሲደርስ ‹‹ፅዳት›› ይደረግላቸዋል፡፡ ዟሂራዊ ፅዳት ማለት ነው፡፡ በመጥረጊያ፤ በመወልወያ፡፡ ይህ ባይከፋም፤ ከዚህ ሁሉ በላይ አንገብጋቢው
መስጂዶችን ከሽርክ እና ቢድዐ ማፅዳት ነው፡፡
ለምሳሌ አንዳንድ መስጂዶች ላይ ‹‹ኹዝ ቢየዲ ያረሱለላህ (አንቱ የአላህ መላክተኛ ሆይ! እጂን ያዙኝ፤ ካለሁበት ጭንቅ አውጡን፤ አጠጡን)›› እና ሌሎች ሽርኮች ይባላሉ፡፡
አንዳንድ መስጂዶች ላይ አሱር ሰላት አዛን ተብሎ ሲያበቃ ኢቃም እስኪል ድረስ 100 ግዜ ‹‹አስተግፊሩላህ›› በጀመዓ (በኢማሙ አውጪነት፤ በመእሙሙ ተቀባይነት) ይባላል፡፡ በተርሃዊ መሃል መሃል የሚባሉ የጀማዓ ዚክሮች፡፡ እነዚህ ቢድዐዎች ናቸው፡፡

ታድያ የአላህ ባርያዎች ሆይ! ሰላት ያለ ጡሃራ እና ዉዱ ተቀባይነት እንደማይኖረው ሁሉ፤ ረመዳንም ይሁን ማንኛውም አምልኮ ከኢኽላስ እና ሱና ውጭ፤ ሽርክ ወይንም ቢድዐን ከቀላቀለ አላህ ዘንድ ተቀባይነት የለውም፡፡

አመድ አፋሽ ላለመሆን እራሳችንን፤ ቤተሰባችንን ከሽርክ እና ቢድዐ እንጠብቅ፡፡ አላህ በሰላም ረመዳን ደርሰው ለእርሱ ብቻ ፆመው፤ ሰግደው፤ ሰድቀው፤ የነብዩን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሱና ተግብረው ሃቁን ከሚወጡት ሰዎች ያድርገን፡፡

የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ ላይ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሀባዎቻቸው፤ ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡