Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የውሸት መጨረሻው (የውሻታም መጨረሻ)

የውሸት መጨረሻው (የውሻታም መጨረሻ)
**********************************
ጃቢር ኢብን ሳሙራ እንዳስተላለፉት፤ የኩፋ ሰዎች ስለ ሳዕድ ለኡመር ቅሬታ አቀረቡለት፤ ኡመርም ሳእድን ከስልጣን አውርዶ አማርን ሾመው፡፡ ስለ ሰዓድ ብዙ ቅሬታዎች አቀረቡ፤ ሰላት በትክክል አይሰግድም እስከማለት ድረስ፡፡
ኡመርም (ለሰዓድ) አስላከበት ‹‹ ዐባ ኢስሃቅ! እነዚህ ህዝቦች በስነስርዓትም አትሰግድም ይላሉ››
አቡ ኢስሃቅ እንዲህ አሉ ‹‹በአላህ ይሁንብኝ! ከአላህ መልክተኛ ጋር ስሰግድ የነበረውን ሰላት ነው ከነሱ ጋር ስሰግድ የነበረው፤ ምንም አልቀነስኩም፡፡ የኢሻን የመጀመሪያዎቹን ሁለት ረከዓዎች አስረዝም እና የመጨረሻዎቹን ሁለቶቹን አሳጥር ነበር››

ኡመር አለ ‹‹የይስሃቅ አባት ሆይ! ይህን ነበር ስላንተ ሳስብ የነበረው›› ከዛም (ኡመር) አንድ ወይንም ከዛ በላይ የሆኑ ሰዎች ከሱ (ከሰዓድ) ጋር ስለሱ ህዝቦችን ለመጠየቅ ወደ ኩፋ አብሮ ላከ፡፡ ወደ (ኩፋም) ዛም ሄዱ አንድም መስጊድ አልቀራቸውም ስለ እሱ ቢጠይቁ እንጂ፡፡ ሁሉም ሰዎች አወደሱት (ስለ ሰዓድ ጥሩን ተናገሩ)፤ ወደ አንድ በኒ አብስ ጎሳ መስጊድ እስኪደርሱ ድረስ፤ አንዱ ኡሳማ ኢብን ቀታዳ የተባለ ቅፅል ስሙ አባ ሰዓዳ የተባለ ሰዉ ቆሞ የሚከተለውን ተናገር፡፡

‹‹በመሃላ እንደጠየቃችሁን ሁሉ ስለ ሰዓድ ልነግራችሁ ግድ ይለኛል
ሰዓድ ከዘማቾች ጋር ዘምቶ አያውቅም፤ የጦር ምርኮም በፍትህ አያከፋፍልም››

ሰዓድ (ይህን ሲሰማ እንዲህ አለ)
‹‹አላህን ሶስት ነገር እጠይቀዋለሁ
አላህ ሆይ! ይህ ባሪያህ ውሸታም ከሆነ ለይዩልኝ ከተነሳ
ረጅም እድሜ ስጠው፤ ድህነቱን ጨምርበት፤ ፈተና ላይ ጣለው››

(እንዳለውም ሆነ) ያሰው ሲጠየቅ እንዲህ ይል ነበር፤ ሽማግሌ እና ፈተና ላይ የወደቀው በሰዓድ እርግማን እንደሆነ ይናገር ነበር፡፡

አብዱል መልኪ ይህንን ሃዲስ ካስተላለፉት ሰንሰለቶች ውሥጥ ዘጋቢ የሆነው እንዲህ ይላል
‹‹ቅንድቦቹ ተሸብሽበው……
መንገድ ላይ የሚያልፉ ትንንሽ ልጃገረድ ሴቶችን ይለክፍ ነበር›› ሰሂሀ አል ቡኻሪ 1 ሙጀለድ፤ 12 ባብ፤ ሃዲስ 722

**********************************
አላህ ከውሸት እና ያለ ማስረጃ ከማውራት ይጠብቀን፡፡