Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሙስሊም ነን ለምንል ሁሉ የተላለፈ ማሳሰቢያ እና ማስጠንቀቂያ በፍጥነት መልክቱን ላልሰሙ

ሙስሊም ነን ለምንል ሁሉ የተላለፈ ማሳሰቢያ እና ማስጠንቀቂያ በፍጥነት መልክቱን ላልሰሙ ወገኖች ማስተላለፍ ግድ ይሎታልመልክቱ ለእኔም፤ ላንተም፤ ላንቺም፤ ለአባትም፤ ለእናቶችም ነው፡፡ 
ምንድን ነው የዛሬውን መልክት ያከበደው እና ያገዘፈው???



ምክንያቱም ፊት ለፊታችን ከባድ መከራ እና ችግር አለ ግን አላየነውም፡፡ 


በአላህ ፈቃድ መጀመሪያ ነፍሴን ቀጥሎ መላውን ማህበረሰብ ይህን ከባድ ለብዙዎች ሊታይ ያልቻለ ችግር መጠቆም ይሆናል፡፡
እሱም ‹‹ሽርክ፤ ጣኦት፤ ኒፋቅ፤ ቢድዓ›› የሚባሉትን ነገሮች በአላህ እዝነት ሳላንዛዛ ለማቅረብ እሞክራለሁ፡፡ 
እውነት ሽርክ የሚባለው ነገር ቀላል ነው ወይ???
ሽርክ በጣም ከባድ ወንጀል፤ ታላቁ የሰው ልጆች ሊሰሩ የሚችሉት በደል ሽርክ ነው፡፡ በጣም የሚያሳዝነው፤ ሙስሊም ነን ብለው እራሳቸውን የሚገምቱ ሰዎች አብዛኛዎቹ፤ ‹‹ላኢላሃ ኢለላህ ሙሃመዱ ረሱሉላህ›› ካሉ ‹‹ሽርክ›› የሚባለው ጉዳይ የሁዳዎችን፤ ነሳራዎችን፤ ሂንዱ እና ቡድሃን ብቻ እንደሚመለከት አድርገው አይፈሩትም፡፡
ከዚህ የከፋ መዘናጋት አነል???
የነብያት ሁሉ አባት፤ ኸሊሉላህ፤ ኢብራሂም (አለይሂ ሰላም) በእጁ የሰባበራቸውን ጣኦታ፤ ግኡዝ አካል የሆኑትን እና ሽርክን በጠቅላላ አስመልክቶ እንዲህ ይላል
‹‹ጌታዬ ሆይ! እኔንም ልጆቼንም ጣኦት ከመገዛት ጠብቀን›› ኢብራሂም በመባል የሚታወቁ ታላቅ ሰለፍ ኡለማ እንዲህ ይላሉ 
‹‹ማን ነው እሱ ከኢብራሂም በኋላ ፈተናን በነፍሴ ላይ አልፈራም የሚል›› ኢብራሂም (አለይሂ ሰላም) አላህ እሳቸውን አስመልክቶ ‹‹ተከተል የአባትህን የኢብራሂምን መንገድ›› ነበር ያለው፡፡ 
የተውሂድ አባት ኢብራሂም ይህን ያህል የሽርክን ፈተና ከእራሱ ላይ እና ከነብያት ልጆቹ ላይ እንዳይደርስ ከፈራ ‹‹እኛስ›› የአላህ ባርያ ሆይ!????????????
ስንቶቻችን ነን ‹‹አላህ ሆይ እኔንም ልጆቼንም ከሽርክ ጠብቀን የምንለው››???ስንቶች ‹‹እውቀት የለኝም፤ ደካማ ነኝ፤ ወንጀል እሰራለሁ›› ብለው ለራሳቸው ያምናሉ፡፡ ‹‹ሽርክ፤ ቢድዐ፤ ኒፋቅ›› ሊኖርብኝ፤ ልሰራ እችላለሁ ብለው በፍፁም አይገምቱም፡፡ 
ታድያ ከዚህ የበለጠ አደጋ ኡማው ላይ የተጋረጠ አለን??? ሽርክን፤ ቢድዐን፤ ኒፋቅን በራስ ላይ አለመፈተሸ፤ አለመጠርጠር እነዚህን የከፉ ተግባራት የሌላ ሰዎች ስራ አድርጎ መመልክት???
እስቲ ጥቂት ምሳሌዎች
1) የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጠዋት እና ማታ እንድናደርግ ካስተማሩን ዚክሮች ውስጥ ‹‹አላህ ሆይ! አንተ ላይ እያወቅኩ ከማጋራት ባንተው እጠበቃለሁ፤ ሳላውቅ ለማጋራው ምህረትህን እጠይቃለሁ››
ልብ እንበል የአላህ ባርያ ጠዋት እና ማታ 3 ግዜ የሚባል ዚክር ነው፡፡ ምንኛ የሽርክ ጉዳይ ቢከፋ ነው ይህን ያህል አፅኖ የተሰጠበት???
2) ከታቢእዬች አንዱ እንዲህ ይላል ‹‹30 የሚሆኑ ሰሃባዎችን አግኝቻለሁ ሁሉም በነፍሳቸው ላይ ንፍቅናን ይፈሩ ነበር››፡፡ በመቀጠል ኡመር ኢብነል ኸጣብ (ረድየላሁ አንሁ) ሁዘይፋን (ረድየላሁ አንሁም) ‹‹ረሱል (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ከጠቀሷቸው ሙናፊቆች ስም ዝርዝር ውስጥ ስሜ አለ ወይ?›› ብሎ ይጠይቀው ነበር፡፡ ስንቶቻችን ነን አላህ ሆይ! ከኒፋቅ ጠብቀን እያልን አላህን አጠብቀን የምንለምን???
3) የአላህ መላክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹‹ለሰሃባዎች›› (ለነዛ ምርጥ ትውልዶች) እንዲህ አሏቸው ‹‹ለኡመቴ የምፈራው ድብቁን ሽርክ ነው›› ምን እንደሆነ ሲጠየቁ ‹‹ይዩልኝ፤ ይስሙልኝ›› አሉ፡፡ ስንቶቻችን ነን ይህን ችግር ለእራሳችን አምጥተን የምንፈትሸ??? 
4) የውመል ቂያማ መጀመሪያ ሂሳብ የሚሰጥባቸው ሰዎች 3 ናቸው ሙጃሂድ፤ አሊም፤ ሃብታም…… ወደ እሳት የሚያስወስዳቸው ወይንም እሳት እንዲገቡ የሚያደርጋቸው ጉዳይ ታላቅ ሽርኮችን ልክ እንደ ‹‹ከአላህ ውጭ ያለን መጣራት፤ ከቀብር ማረድ፤ ጥንቆላ›› ሳይሆን ስራቸውን እነዚህን ታላላቅ ተግባራት ‹‹ይዩልኝ፤ ይወቁልኝ›› ስለጨመሩበት እና ለአላህ ብቻ ጥርት ብሎ ስላልተሰራ ነው፡፡
5) ስለ ሽርክ ሲገልፁ የአላህ መላክተኛ ‹‹ጨለማ ክፍል ውስጥ እንዳለ ጥቁር ድንጋይ፤ እዛም ላይ እንደሚሄድ ጉንዳን›› እንመልክት የአላህ ባርያዎች እነዚህን ከባድ እኛ ልብ ብለን የማናያቸው ከባባድ አደጋዎች፡፡
6) ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ‹‹ከሰረ የዱንያ አምላኪ ባርያ….›› ብለዋል፡፡
7) ስንቶች ይሆኑ ‹‹ዛሬ አይቀናኝም…..›› እያሉ በገድ የሚያምኑት???
8) ቢድዐ፤ ቢድዓን ‹‹አኽባሽ ወይንም ሱፊ›› ነው የሚሰሩት ብሎ ከማሰብ እያንዳንዱን ስራችንን ‹‹ቢድዐ›› አለው ወይንስ ከምንድን ነው ማስረጃዬ ብለን እንፈትሽ፡፡ ስንት እና ስንት የቢድዐ አይነቶች ሰዎች በስሜት ተነድተው እየሰሩት ይገኛሉ፡፡ አንድም ቀን ሰው እራሱን ለመጠየቅ ዝግጁ ካላደረግ፤ ሌሎችን ከሚወቅስበት ወንጀል በላይ ሰርቶ ሊገኝ ይችላል፡፡

ስንቶች ይኖራሉ ሽርክ ሲባል የሁዳ፤ ነሳራ፤ ቡዲስቶቾ፤ ሂንዱ፤ ገጠር ያሉ ሰዎች፤ እናት እና አባቶች ብቻ አድርገን የምናየው፡፡ ስንቶች ይሆኑ ኒፋቅ የሚለውን ቃል ለሆኑ ሰዎች ብቻ እንደሆነ እና እራሳቸውን እንደማይመለከታቸው አድረገው የሚወስዱ፤ ስንቶች ይሆኑ ቢድዐ ሲባል አንድ ጫት በአፉ ላይ ይዞ ሙስበሃ አንገቱ ላይ 1000 አንጠልጥሎ የሆነ ሰው ላይ ብቻ የሚለጥፉት???
ይህ ሲባል ደግሞ በግልፅ ቢድዐ እና ሽርክ የሚሰሩ ሰዎችን ዝም እንበል ማለት አይደለም፡፡ ይህ ሊሰመርበት ይገባል፡፡ ከነእርሱ መጠንቀቅ እና ማስጠንቀቅ ዋጂብ (ግዴታ) ነው፡፡
የአላህ ባርያዎች ሆይ! ነፍሴን በመጀመሪያነት ከዛም እናንተን በጣም የዚህን መልክት ግዙፍነት አውቀን፤ ነብያት እራሳቸውን አላህ ከሽርክ እንዲጠብቃቸው እንደለመኑት እኛም ግዝፈቱን አይተን አላህን እኛንም ልጆቻችንም እንዲጠብቀን እንለምነው፡፡
አላህ ከሽርክ፤ ከኒፋቅ፤ ከቢድዐ ይጠብቀን፡፡ በነብያት መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በሰሃባዎቻቸው እና ሃቅ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡