Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ስለ አላህ የማያውቁትን መናገር ወንጀል ነው



=======================ሙሃመድ አወል መንዙማ ላይ ስለ አላህ የማያውቀውን እንዲህ ስል ይናገራል፡፡ አላህ ይጠብቀን
‹‹የቃጥባሬው ጌታ ኢሳ የአላህ ኑርከሚን ኢንደላሂ (ከአላህ ዘንድ) የተባለ አብሽር››
እገሌ አብሽር ተባለ፤ ማለት የሚቻለው መቼ ነው???ከአንደበታቸው የማይናገሩት የመጨረሻው ነብይ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በወህይ አማካኝነት፤ አቡበክር፤ ኡመር፤ ኡስማን፤ አልይ፤ ጠለሃ፤ ዙበይር እና የመሳሰሉትን (ረድየላሁ አንሁም) ሰሃባዎች የጀነት መሆናቸውን አበሽረዋል፡፡ከዚህ ውጭ እሳቸው ሞተዋል፡፡ በእርሳቸው ሞት ደግሞ ወህይ ተቋርጧል፡፡ አላህ ደግሞ በተከበረው ቁርዓኑ ላይ በጥቅል አማኞችን አብሽሩ ብሏል አላህ ከአማኞች ያድርገን፡፡
የማያውቁትን በአላህ ላይ መናገርን አስመልክቶ አላህ እንዲህ ይላልጌታዬ እርም ያደረገው መጥፎ ሥራዎችን፣ ከርሷ የተገለጸውንና የተደበቀውን ኃጢኣትንም፣ ያላግባብ መበደልንም፣ በርሱም ማስረጃ ያላወረደበትን ጣዖት በአላህ ማጋራታችሁን፣ በአላህም ላይ የማታውቁትን መናገራችሁን ነው» በላቸውላመኑ ሰዎች በጥቅሉ አላህ ይማራቸው እንላለን፡፡ እገሌ ከአላህ ዘንድ እንዲህ ተባለ ግን አንልም፡፡ አላህ ይጠብቀን