Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ቀብር እና ስርዓቱ በአጭሩ


by Sadat Kemal Abu Nuh

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ ሩህ ሩሀ በሆነው የአላህ ሶላት እና ሰላም በአሽረፈል ከልቅ እና የሣቸውን ፈለግ በተከተለ ላይ ይሁን:: 
ቀብር እና ስርዓቱ
ኮልፌ ኮልፌ ወይንስ መርካቲ መርካቶ
ቀብር ላይ የሚሰሩ ቢድዓዎች
እኛ ከሰሃባዎች እና ሰለፎቻችን በላይ አዋቂ እና አላህን ፈሪ ነን???

ቀብርን መዘየር የሚቀጥለውን አለም ለማስታወስ እና ለእሱም ዝግጁ ለመሆን ይጠቅማል፡፡ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም)ኡመታቸውን ያላሳዩት፤ ያመከሩት ነገር የለም ለኡማው ከሚጠቅመው ጠቁመው፤ የሚጎዳውን አስጠንቅቀው፡፡

ታላቁ ሰሃባ፤ ሶስተኛው ኸሊፋ ኡስማን ኢብን አፋን (ረድየላሁ አንሁም) ቀብር ሲያዩ በጣም ያለቅሱ ነበር፡፡ ለምን ተብለው ሲጠየቁ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ሲሉ ሰምቼያለሁ ‹‹ቀብሩ ያማረለት ከዛ በኋላ ያለው ህይወቱ ያምርለታል………..››

ለአእምሮ ባለቤቶች ሰው ሲቀበር ማየት እንዲያስተነትኑ የሚያደርግ ጉዳይ ነበር፡፡ ዛሬ ዛሬ ቀብር ቦታዎች ስለ ንግድ እና ፖለቲካ እና ሌሎች ጉዳዩችን ማውሪያዎች እየሆኑ ነው፡፡
ኮልፌ መርካቶ እስኪመስል ድረስ ግማሹ ስልኩን አውጥቶ ጮክ ብሎ ጫንከው አወረድከው እያለ ያወራል፤ ግማሾች 2 እና ሶስት ወይንም በቡድን ሆነው፤ ስለ ቆጥ የባጡን ያወራሉ፤ ፊታቸውን ለሟች ቤተሰብ ለማሳየት ብቅ ብቅ ያ የሚመስሉም አይጠፉም፡፡

የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ምን ነበር ያደረጉት???

በራ ኢብን አዚብ (ረድየላሁ አንሁም) የተባሉት ሰሃባ እንዲህ ይላሉ ‹‹ከአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ጋር ወደ አንድ የአንሷር ሰው ቀብር ሄድን፡፡ (የቀብር) ቦታው ላይ ስንደርስ እና ሪሳው ውስጥ ሲገባ፤ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ወደ ካእባ እቅጣጫ ዞረው ተቀመጡ፡፡ እኛም ሁላችንም እሳቸውን ከበን ተቀመጥን፤ ወፍ አናታችን ላይ ሳይረበሹ የተቀመጡብን ያህል፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በእጃቸው እንጨት ይዘው ነበር መሬቱን ጫር ጫር እያደረጉበት፡፡ ሶስት ግዜ ወደ ሰማይ ቀና እያሉ ወደ መሬትም አቀረቀሩ ከዛም

‹‹ከቀብር ቅጣት በአላህ ተጠበቁ›› አሉ
ከዛም እሳቸው እንዲህ አሉ

‹‹አላህ ሆይ! ከቀብር ቅጣት ባንተ እጠበቃለሁ››
ይህንንም ሶስት ጊዜ አሉት
…………….
ሌላም ብዙ ትምህርት አስተማሩ
በመቀጠል፤ ቀብር ላይ ሄዶ አኸይራን ከማስታወስ ውጭ ወሬ እና ዛዛታ እንደማይገባው ሁሉ፤ ቀብር ላይ የሚሰሩ በሸሪዓው ከነብያችንም፤ ከሳሃባዎችም ከቀደምት ሰለፉነ ሷሊሁን ያልተገኙ ነገሮች የሚሰሩ ሰዎች አሉ፡፡

ቢድዓዎቹ ምንን ይመስል
1) ያሲን እና የተለያዩ ቁርዓኖችን በጀመዓ መቅራት፤-
2) የሞተውን ሰውዬ ‹‹አብደላ አሁን መላኢካዎች መጥተው ጌታህ ማን ነው ብለው ይጠይቁሃል፤ አላህ በላቸው፤ ዲንህ ምንድን ነው ይሉሃል፤ ኢስላም በላቸው፤ በናንተ መሃል የተላከ ሰው አለ ይሉሃል፤ ነብዩ ሙሃመድ በላቸው›› ብሎ ወደ ቀብሩ ጮሀው መናገር እና የመሳሰሉት

ጥቂት መልሶች
1) ቁርዓን ቀብር ላይ መቅራት ከነብያችንም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ይሁን ከኹለፋኡ ራሺዲን (ሪድዋኑላሂ አለይሂም)፤ ከሙሃጂሮች፤ ከአንሳሮች፤ ከሶስቱ ምርጥ ትውልድ አላገኘነውም፡፡ ታድያ ይህ ብቻ በቂ አይደለምን ይህ ነገር ቢድዓ፤ ወይንም ዲን ላይ የተጨመረ ፈጠራ ለመሆኑ???? ፈጠራ ሁሉ ጥመት ነው፡፡

ቁርዓን ደግሞ እንዴት መቀራት እንዳለበት ሁኔታውን አላህ አልተናገረምን፤ ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አላሳዩምን

አንዱ ሰው ቁርዓን ሲቀራ ሊሎች ማዳመጥ ነው ያለባቸው፡፡ ይህ ነው በሸሪዓ የመጣው፡፡ ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንኳን ጂብሪል ሲቀራ ዝም ብለው ያዳምጡት ነበር፡፡ ታላቁ ሰሃባ ኡበይ ኢብን ካዕብም (ረድየላሁ አንሁም) ሲቀራባቸው ዝም ብለው ያዳምጡ ነበር እንጂ አንድ ላይ መቅራት አልመጣም፡፡

2) ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) አንድ ሰው ቀብራችሁት ከጨረሳችሁ በኋላ ትንሽ ቆየት በሉለት እና አላህ ፅነት እንዲሰጠው ለምኑለት እንጂ ያሉት የሚጠየቀውን ጥያቄ እና መልስ ንገሩት አሉን?????
አረ የአላህ ባሪያዎች ሆይ! አላህን እንፍራው ሰሃባዎች እና ሰለፎቻችን እኮ አላህ ዘንድ የተወደዱት መልክተኛው (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ያሳዩዋቸውን ነገር ብቻ በመከተላቸው እና ምንም ባለመጨመራቸው ነው፡፡

እኛ ከሰሃባዎች በላይ ኢስላምን አውቀን ነው፤ ዲኑ ላይ ድሪቶ የምንደራርብበት???
አላህን እንፍራ ሁሉም ቢድዓ ጥመት ነው፤ ሁሉም ጥመት የእሳት ነው፡፡
ኮልፌ ሞትን ማስታወሻ እንጂ ትርፍ ዛዛታ ወሬ ማውሪያ አይደለም፤ ቀብሮች ልክ እንደሌላው የሃይማኖት ድንጋጌ ምን መሰራት እንዳለበት የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እና ሰሃባዎቻቸው ሰርተው አሳየተውናል እሱን ብቻ እንከተል፤ ቁርዓንም መቅራት ይሁን ሌላ ነገር የለም፡፡

የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያችን፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረቦቻችን እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡