Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አላህ የረገማቸው፡፡


አልይ ኢብን አቢ ጧሊብ (አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና) እንዳስተላለፉት የአላህ መልክተኛ (ሰላትና ሰላም በርሳቸው ላይ ይሁንና) አራት ሰዎችን አላህ ረግሟቸዋል አሉ
1)‹‹አላህ ረግሞታል ከአላህ ሌላ ላለ ያረደ፤ 
2)አላህ ረግሞታል በሀይማኖት መሰረት የሌለውን ነገር ያመጣን ሰው ከለላ የሰጠ (ሙብተዲን ያስጠጋ) 
3)አላህ ረግሞታል ወላጆቹን የሚረግም (ያስረገመ)፤
4)አላህ ረግሞታል በመሬት ላይ የተቀመጠን ምልክት የቀየር (በሁለት ሰዎች መካከል ያለውን መሬት ምልክት የቀየረ)››
ኢማሙ ሙስሊም ዘግበውታል፡፡ አላህ ሆይ! ከነዚህ የሚያስረግሙ ተግባራት ባንተ እንጠበቃለን፡፡ አላህ ሆይ! ሀቅን አሳየን እንድንቀበለውም አድርገን፤ ጥመትንም (ባጢልንም) አሳየን እንድንርቀው አድርገን፡፡