Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ኢኽዋኖች ሱዳን ላይ……


by Sadat Kemal Abu Nuh

بسم الله الرحمن الرحيمالحمد لله رب العالمين، وصلى الله وسلم على رسوله
ብዙውን ማውራት አያስፈልግም ዋናው ነጥብ በቂ ነው፡፡ ታሪኩ ይህን ይመስላል፡፡ ሱዳን ውስጥ ከበፊት ጀምሮ ተውሂድ በማስተማር የሚታወቁት አቡ ዘይድ የተባሉ ታላቅ መሻኢህ አሉ (አላህ ይጠብቃቸው)፡፡ የኢኽዋን ፖለቲካ ድርጅት አራማጅ የነበረው የጥመት መሪ፤ ዶክተር ሀሰን አቱራቢ እንዲህ ሲል ነገራቸው‹‹እኛ ስልጣን ላይ ስንወጣ ሁሉንም ቀብር አፍርሰን አንዲት ቀብር ብቻ እንተውላችኋለን፡፡ እናንት ሁሌ ቀብር አታምልኩ ስለሆነ የምትሉት በዛች ቀብር ቢዚ ትሆናላችሁ›› አላቸው፡፡እውነታው ግን አደለም ቀብር አምልኮ ሊያስቆሙ፤ ቀብር ማምለክ ሽርክ ነው ብለውም ትንፍሽ አይሉም፤ ቲፎዞ ስለሚቀንስባቸው፡፡ ከዚህም አልፎ ስንት እና ስንት ቀብሮች ሱዳንም ላይ ይሁን፤ የዚህ ፖለቲካ ድርጅት መመስረቻ አገር ግብፅ ላይ ይገኛል፡፡
በጣም የሚገርመው የነበረውን ንጉስ ገልብጠው ስልጣን ሲይዙ፤ አደለም ቀብር አምልኮን ሊያፈርሱ፤ በስልጣን ተጣልተው፤ መሪው ሀሰን ቱራቢን እስር ቤት አስገባው፡፡
ከዚህ ሁሉ በጣም የሚገርመው ግን፤ ኢኽዋነል ሙስሊሚን ስልጣን ጥማት ያለበት የፖለቲካ ድርጅት፤ ነብያት ሁሉ የሚያስጨንቃቸው ተውሂድ፤ አላህ ጥሪ ይጀመርበት ያለው የተውሂድ አርእስት አያሳስባቸውም፡፡ አሳዛኝ ክስተት ሱዳን ውስጥ ልጨምር፡፡
ቤተመንግስቱ አካባቢ መንገድ ሊሰራ ይፈለግ እና አንድ የሚመለክ ቀብር እዛ አካባቢ አለ፡፡ ኢንጂነሮች ይህ ቀብር ይነሳ መንገዱን ለመስራት ሲሉ፤ ቀብሩን ማን ደፍሮ ያንሳው በሚል ሲመከር ቆየ፡፡ ሁሉም ፈሩ ከዛም የተውሂድ ታጋይ የሆኑት ሸይኽ አቡ ዘይድ (ሀፊዘሁላህ) እንዲያነሱት ተጠየቁ፤ ከዛም አልሃምዱሊላህ ምንም ሰዎች እንደፈሩት ሳይሆኑ ቀብሩን ከቦታው ላይ አነሱት፡፡
ይህቺ ናት ሱዳን ታላላቅ የሽርክ እና የኩፍር ተግባር የተሞላባት፡፡ ግብፅ ስትሂድ የአህመድ በደዊ፤ ነፊሳ፤ ሁሴን እና የመሳሰሉት እየተባለ ሰው ሽርክ ሲሰራ፤ ይህን ለሙስሊሞች ቆሚያለሁ እያለ ‹‹የሚያታለውን›› የፖለቲካ ድርጅት፤ ሰዎች ዘላለም እሳት ውስጥ የሚከታቸው ነገር አይጨንቀውም፡፡
ታድያ ጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪ የሚያስደርገው ሽርክ የማይጨንቀው ኢኽዋን ‹‹አታላዩ›› እውነት የኡማው ጉዳይ ይጨንቀዋል???
ነቃ በል የአላህ ባርያ! የነብያትን ፈለግ የማይከተል ለድል አይበቃም፡፡ ከነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በላይ ለአማኞች አዛኝ የለም፡፡ እሳቸው ከተውሂ ጀመሩ፤ ለተውሂድ ሲሉ ለፉ፤ ከመሞታቸው በፊት ኡማቸውን ስለ ሽርክ አስጠነቀቁ፡፡ ታድያ ነብያችንን ተቃርነው አለም ላይ ስንት የፖለቲካ ድርጅቶች እስልምናን የፖለቲካ ማራመጃቸው በማድረግ፤ የነብያትን መንሃጅ ትተው እውነት ድል ያገኛሉ፡፡ አለም ላይ ስንት ቀብር ይመለካል፡፡ ያውም እነዛ የቀብር ባለቤቶች የጀነት ይሁኑ የጀሃነም ገና ያልተመሰከረላቸው፡፡ የድል ባለቤቶች እስከቂያማ ድረስ የነብያትን መንሃጅ የሚከተሉ ናቸው፡፡
አላህ ሆይ! የዲን ግንዛቤ ስጠን፡
በጣም የሚገርመው የነበረውን ንጉስ ገልብጠው ስልጣን ሲይዙ፤ አደለም ቀብር አምልኮን ሊያፈርሱ፤ በስልጣን ተጣልተው፤ መሪው ሀሰን ቱራቢን እስር ቤት አስገባው፡፡ ከዚህ ሁሉ በጣም የሚገርመው ግን፤ ኢኽዋነል ሙስሊሚን ስልጣን ጥማት ያለበት የፖለቲካ ድርጅት፤ ነብያት ሁሉ የሚያስጨንቃቸው ተውሂድ፤ አላህ ጥሪ ይጀመርበት ያለው የተውሂድ አርእስት አያሳስባቸውም፡፡ አሳዛኝ ክስተት ሱዳን ውስጥ ልጨምር፡፡ቤተመንግስቱ አካባቢ መንገድ ሊሰራ ይፈለግ እና አንድ የሚመለክ ቀብር እዛ አካባቢ አለ፡፡ ኢንጂነሮች ይህ ቀብር ይነሳ መንገዱን ለመስራት ሲሉ፤ ቀብሩን ማን ደፍሮ ያንሳው በሚል ሲመከር ቆየ፡፡ ሁሉም ፈሩ ከዛም የተውሂድ ታጋይ የሆኑት ሸይኽ አቡ ዘይድ (ሀፊዘሁላህ) እንዲያነሱት ተጠየቁ፤ ከዛም አልሃምዱሊላህ ምንም ሰዎች እንደፈሩት ሳይሆኑ ቀብሩን ከቦታው ላይ አነሱት፡፡ይህቺ ናት ሱዳን ታላላቅ የሽርክ እና የኩፍር ተግባር የተሞላባት፡፡ ግብፅ ስትሂድ የአህመድ በደዊ፤ ነፊሳ፤ ሁሴን እና የመሳሰሉት እየተባለ ሰው ሽርክ ሲሰራ፤ ይህን ለሙስሊሞች ቆሚያለሁ እያለ ‹‹የሚያታለውን›› የፖለቲካ ድርጅት፤ ሰዎች ዘላለም እሳት ውስጥ የሚከታቸው ነገር አይጨንቀውም፡፡ታድያ ጀሃነም እሳት ውስጥ ዘውታሪ የሚያስደርገው ሽርክ የማይጨንቀው ኢኽዋን ‹‹አታላዩ›› እውነት የኡማው ጉዳይ ይጨንቀዋል???ነቃ በል የአላህ ባርያ! የነብያትን ፈለግ የማይከተል ለድል አይበቃም፡፡ ከነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በላይ ለአማኞች አዛኝ የለም፡፡ እሳቸው ከተውሂ ጀመሩ፤ ለተውሂድ ሲሉ ለፉ፤ ከመሞታቸው በፊት ኡማቸውን ስለ ሽርክ አስጠነቀቁ፡፡ ታድያ ነብያችንን ተቃርነው አለም ላይ ስንት የፖለቲካ ድርጅቶች እስልምናን የፖለቲካ ማራመጃቸው በማድረግ፤ የነብያትን መንሃጅ ትተው እውነት ድል ያገኛሉ፡፡ አለም ላይ ስንት ቀብር ይመለካል፡፡ ያውም እነዛ የቀብር ባለቤቶች የጀነት ይሁኑ የጀሃነም ገና ያልተመሰከረላቸው፡፡ የድል ባለቤቶች እስከቂያማ ድረስ የነብያትን መንሃጅ የሚከተሉ ናቸው፡፡አላህ ሆይ! የዲን ግንዛቤ ስጠን፡