Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሰማይ እና ምድርን የፈጠሩት የአብሬት ሸህ ናቸውን?

by Sadat Kemal Abu Nuh

‹‹…ሰማይ እና ምድርን የፈጠሩት የአብሬት ሸህ ናቸውን?››
አንድ መስጂድ ላይ ስለ ሽርክ አስከፊነት አስተምሬ ነበር፡፡ እዛ ትምህርት ውስጥ አብሬት አካባቢ ስለሚሰራው ሽርክ ጠቅሼ ነበር፡፡ ትምህርቱን ሲከታተል የነበረ ወጣት ትምህርቱ ካለቀ በኋላ የሚከተለውን አለኝ ‹‹ያለከው ሁሉ ልክ ነው፡፡ እኔ እናቴ አብሬት ሸህ መቃብር ይዛኝ ሄደች፡፡ለበረካውም ጭቃ ላይ በቂጥህ ቁጭ በል አለችኝ፡፡ከዛም ጠየቅኳት፡፡እናቴ ሆይ! ሰማይ እና ምድርን የፈጠሩት የአብሬት ሸህ ናቸውን?››እሷም‹‹አዎን›› አለችኝ፡፡**************************************************ይህ የአገራችን ኢትዬጵያ ሁኔታ በከፊሉ ነው፡፡ የሽርክን አስከፊነት ሳያስተምሩ እና ወደ ተውሂድ አርእስት ሳይጣሩ ወደ ሌላ አርእስት መግባት ያስወቅሳል፡፡ አላህ እና መልክተኛውም አደራ ያሉበትን ማፍረስ እና አደራ መብላት ነው፡፡ እያንዳንዱ ባለሙያ ሙያው የሚያስገድደውን መስራት አለበት፡፡ ለምሳሌ አንድ ዶክተር ልቡን ለታመመ ሰው የጨጓራ መድሃኒት ቢሰጥ ‹‹የዶክተርነት ፍቃዱ ይቀማ›› ይባላል፡፡ ወደ አላህ መንገድ ዳእዋ የሚያደርጉ ሰዎች የመጀመሪያ ጥሪያቸው ነብያት ሁሉ የጠሩበትን ተውሂድ እና ከሽርክ ማስጠንቀቅ መሆን አለበት አለበለዚያ የነብያትን መንሃጅ አልተከተለም፡፡ ለዳእዋም ብቁ አይደለም፡፡ ገና እራሱ ዳእዋ ሊደረግለት ይገባል፤ የተውሂድን ትልቅነት ስላላወቀ፡፡የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያት መደምደሚያ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረቦቻቸው እና ፈለጋቸውን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡