Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ሼባው እና አሮጊቷ ጨቅጫቃ ሆነዋ

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን‹‹ሼባው እና አሮጊቷ ጨቅጫቃ ሆነዋል›› ድሮ ግን አፋችንን ከመፍታታችን በፊት፤ ከምንም ነገር በፊት ‹‹ማማ፤ ባባ›› የሚሉትን ብቻ ነበር የምናውቀው፡፡ ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂኡን
ቀጥታ ወደ አርስቱ እንግባ፡፡ አላሁ (ሱብሃነሁ ወተዓላ) ከራሱ ሃቅ ቀጥሎ ያስቀመጠው ‹‹የወላጅን ሃቅ›› ነው፡፡ አባት እና እናት ልጆቻቸውን ሲያሳድጉ ያድግልኛል ብለው በትልቅ ተስፋ እና ደስታ፤ ከከባድ እንክብካቤ ጋር ልጆችን አሳደጉ፡፡
‹‹እናት›› በተለይ ‹‹አይጠየፊ›› የሚባል ስም አላት፡፡ ማንም እናት የልጇን ቆሻሻ ሰገራም ይሁን ሽንት አትጠየፍም፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ የሚገርመው፤ ህፃናት አፍንጫቸውን ‹‹ንፍጥ›› ቢደፍነው፤ ተናፍጠው ማውጣት ስለማይችሉ ‹‹አይጠየፊ እናት›› በአፏ መጣ ታወጣዋላች፡፡ አላህ ኸይር ጀዛዋን ይክፈለው፡፡
አላህ የሰውን ልጅ በተለያየ እድሜ እና ባህሪ ቀርፆታል፡፡ እድሜው እየገፋ ሲሄድ፤ መርሳት፤ መበሳጨት፤ ያለ ነው፡፡ በጣም የሚገርመው፡፡ አባት እና እናት ልጃቸውን መቼም ቢሆን ‹‹ልጄ›› በሚል የክብር ስም ሲጠሩት፤ የሰው ልጅ በተለይ በዚህ ዘመን ያለ ወጣት ምን ነክቶት ነው፤ የገዛ አባት እና እናቱን ‹‹ሼባው እና አሮጊቷ›› እያለ የሚጠራው፡፡

አንድ አስተማሪ የሰማሁትን ትምህርት ካፍላችሁ፡፡ አንድ ሴት ከእናቷ ጋር ነበር የምትኖረው፤ እናትየው እድሜዋ ገፍቶ እቃ ሁሉ መስበር ጀምራለች፡፡ ይህቺ ሴት ወጣት ልጅ አላት፡፡ ልጇን ሄድ እና ገበያ ለእናቴ የሚሆን ፕላሲቲክ ኩባያ ይዘህ ና አለችው፡፡ እሱም ሁለት ገዝቶ መጣ፡፡ እናቱም ጠየቀችው ‹‹እኔ ያልኩህ አንድ ነበር›› ወጣቱም እንዲህ ሲል መለሰት ‹‹አንዱ ለእናትሽ ነው፤ አንዱ ደግሞ አንቺ ስታረጂ ነው››

ልብ ልንል የሚገባው ዛሬ ምንም የማያውቁ ኋላ ቀር የሚመስሉን አባት እና እናቶቻችን በዘመናቸው እና በኖሩበት ማህበረሰብ አዋቂ፤ ብልጥ እና ማህበረሰቡ ውስጥ ታይቶ የማይጠገብ ውበት ነበራቸው በዘመናቸው፡፡ ዛሬ የእኛ አባት እና እናቶች በግድ እኛ የለበስነውን ‹‹ጂንስ እና ጉርድ›› ካለበሱ ከነሱ ጋር አብሮ መሄድ ይከብደናል የሚሉ ወጣቶች ሞልተዋል፡፡

በጣም የሚገርመው አንዳንድ በዚህ ግዜ ያሉ ወጣቶች የሚከተለው ችግሮች ይታይባቸዋል
1) ከእናት ከ አባቱ ጋር አብሮ መሄድ እና ከተማ ላይ መታየት ማፈር
2) አባት እና እናቱን መሳደብ እና መገላመጥ
3) ፍርድ ቤት ላይ እናቱን ደብድቦ ያየሁት ካፊር አለ፡፡ የካፊሩ ላይበቃ እናቱን ‹‹እገድላለሁ›› ያለ የጫት ሱሰኛም አለ፤ ይህም በማስረጃ፡፡
ክብር ለ‹‹የአደጋ ጌዜ ተጠሪ›› በመባል ለሚታወቁት እናት እና አባት፡፡ ነገ የእኛ ልጆች ምን ሊያደርጉን ይችላሉ???

ሰው የሰራውን ያጭዳል፡፡
ቤተሰቦቻችን እኛን ሲያሳድጉን ‹‹ያድግልኛል›› በሚል ንያ ነው፤ ዛሬ ‹‹ሼባው እና አሮጊቷ›› እየተባለ ይሞታሉ በሚል ንያ ይሆን??? አላህ ይጠብቀን፡፡ አላህ ሆይ! የወላጆቻችንን መብት ከሚያከብሩት አድርገን፡፡