Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የአደም ልጅ ሆይ! ክብርህን አስጠብቅ!!!!!

    by Sadat Kemal Abu Nuh

۞ وَلَقَدْ كَرَّمْنَا بَنِىٓ ءَادَمَ وَحَمَلْنَٰهُمْ فِى ٱلْبَرِّ وَٱلْبَحْرِ وَرَزَقْنَٰهُم مِّنَ ٱلطَّيِّبَٰتِ وَفَضَّلْنَٰهُمْ عَلَىٰ كَثِيرٍ مِّمَّنْ خَلَقْنَا تَفْضِيلًا የአደምንም ልጆች በእርግጥ (ከሌላው ፍጡር) አከበርናቸው፡፡ በየብስና በባህርም አሳፈርናቸው፡፡ ከመልካሞችም (ሲሳዮች) ሰጠናቸው፡፡ ከፈጠርናቸውም ፍጡሮች በብዙዎቹ ላይ ማብለጥን አበለጥናቸው፡፡
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوٓا۟ إِنَّمَا ٱلْمُشْرِكُونَ نَجَسٌ فَلَا يَقْرَبُوا۟ ٱلْمَسْجِدَ ٱلْحَرَامَ بَعْدَ عَامِهِمْ هَٰذَا ۚ وَإِنْ خِفْتُمْ عَيْلَةً فَسَوْفَ يُغْنِيكُمُ ٱللَّهُ مِن فَضْلِهِۦٓ إِن شَآءَ ۚ إِنَّ ٱللَّهَ عَلِيمٌ حَكِيمٌ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! አጋሪዎች እርኩሶች (ነጃሳዎች) ብቻ ናቸው፡፡ ከዚህም ዓመታቸው በኋላ የተከበረውን መስጊድ አይቅረቡ፡፡ ድኽነትንም ብትፈሩ አላህ ቢሻ ከችሮታው በእርግጥ ያከብራችኋል፡፡ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና፡፡
حَتَّىٰٓ إِذَا جَآءَ أَمْرُنَا وَفَارَ ٱلتَّنُّورُ قُلْنَا ٱحْمِلْ فِيهَا مِن كُلٍّ زَوْجَيْنِ ٱثْنَيْنِ وَأَهْلَكَ إِلَّا مَن سَبَقَ عَلَيْهِ ٱلْقَوْلُ وَمَنْ ءَامَنَ ۚ وَمَآ ءَامَنَ مَعَهُۥٓ إِلَّا قَلِيلٌ ትእዛዛችንም በመጣና እቶኑም በገነፈለ ጊዜ «በእርሷ ውስጥ ከየዓይነቱ ሁሉ ሁለት ሁለት (ወንድና ሴት) ፤ ቤተሰቦችህንም ቃል ያለፈበት ብቻ ሲቀር ያመነንም ሰው ሁሉ ጫን» አልነው፡፡ ከእርሱም ጋር ጥቂቶች እንጂ አላመኑም፡፡
ከላይ ካየናቸው አንቀፆች ውስጥ የሚከተለውን ትምህርት እንወስዳለን፡፡ 
1) አላህ የአደምን ልጅ አከበረው፤ ከሌሎች ፍጡራን ሁሉም አላቀው 
2) ይህ ክብሩ ሊጠበቅለት የሚችለው አላህን በብቸኝነት በማምለክ ብቻ ነው፡፡ ይህን ካላደረገ እርኩስ የሚያስብለውን ተግባር ፈፅሟል 
3) ክብሩን ሳያስጠብቅ ከቀሩ፤ ከእንስሳ በታች ሁሏ የሚሆንበት ግዜ አለ፡፡ የመጨረሻው አንቀፅ እንደሚጠቅሰው፡፡ ከ(እንስሳትም) ጥንድ ጥንድ (ወንድ እና ሴት) እና ያመኑት የኑህ ህዝቦች ብቻ መርከቧ ላይ ተጭነው ነፃ ሲወጡ ያለመኑት ደግሞ ከባድ ቅጣት አጋጠማቸው፡፡
የአደም ልጅ ሆይ! አላህ አክብሮህ ሲያበቃ፤ ክብርህን በተውሂድ ብትጠብቅ ይሻልሃል፡፡ ይህን አላደርግም ካልክ ሁለት አገር ውርደት ያጋጥምሃል፡፡
ይህ መልክት ከነፍሴ ጨምሮ ለሁሉም የእምነት ወንድም እና እህቶቼ የተላለፈ ይሆናል፡፡የአላህ ሰላት እና ሰላም በአላህ ውድ ነብይ ላይ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረባዎቻቸው እና ፈለጋቸውን በተከተለ ሁሉ ላይ ይሁን፡፡ አላሁመ አሚን፡፡