Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

LOL (Laugh Out Loud) ከት ብለው ይሳቁ

by Sadat Kemal Abu Nuh

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ እጅግ በጣም ሩህሩህ፡፡ የአላህ ሰላት እና ሰላን በነብያት መደምደሚያ ላይ፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረባዎቻቸው እና የነሱን ፈለግ በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡በመቀጠል፤ የአላህ መልክተኛ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹እኔ የማውቀውን ብታውቁ ኖሮ ትንሽ ስቃችሁ፤ ብዙ ታለቅሱ ነበር››፡፡ ይህ አባባል እንግዲህ ከምርጦች ሁሉ ምርጥ፤ አላህን ፈሪ የሆኑት ነብያችን የተናገሩት ንግግር ነው፡፡ ዛሬ ዛሬ facebook and social media ላይ LOL (Laugh out loud)
‹‹ከት ብለው ይሳቁ›› የሚባለው አባባል እያንዳንዱ ኮሜንት እና ፖስቶች ላይ ሙስሊሞች የሚጠቀሙት የተለመደ ቃል ሆኗል፡፡ ምን ይሆን እንደዚህ ‹‹ከት ብለው ይሳቁ›› የሚያስብለው፤ አንዱ ስለ ሽርክ አስከፊነት የተደረገ ፖስት ላይ LOL (Laugh out loud) ‹‹ከት ብለው ይሳቁ›› ብሎ ይፅፋል፤ አንዱ አንዷን ሴት ይተርብ እና ወይንም ያበሽቅ እና እሷ ገብታ LOL (Laugh out loud) ‹‹ከት ብለው ይሳቁ›› ብላው ትወጣለች፡፡ ምነው የተፈጠርንበትን አላማ ረሳን??? እስቲ ሁላችንም ከእኔ ጀምሮ፤ ነብያችን እና ሰሃባዎቻቸው ሲያደርጉ እንደነበርው አላህን ፈርተን ያለቀስንባቸውን ግዚያት እስቲ እናስታውስ፤ በቅርብ ግዚ ውስጥ መቼ ነው ወደ አላህ በፀፀት እና በለቅሶ ሱጁዴን ያሳመርነው ብለን እራሳችንን እንጠይቅ፡፡ በጣም የሚያሳዝነው ግን ፊልም፤ ኳስ፤ ዘፈን እና የመሳሰሉትን ቀልብ አድራቂ ነገሮች ተረስተው፤ ማልቀሱ ቀረና በትንሽ በትልቁ LOL (Laugh out loud) ‹‹ከት ብለው ይሳቁ›› LOL (Laugh out loud) ‹‹ከት ብለው ይሳቁ›› LOL (Laugh out loud) ‹‹ከት ብለው ይሳቁ›› ይባል ጀመር፡፡ ሳቅ ማብዛት ልብ ያደርቃል ሲባል ሰምቼ ነበር፡፡ አላህ ሆይ! ወደ ነብያችን እና ባልደረቦቻቸው ተግባር እና እምነት መልሰን፡፡ በጠላቶቻችን ላይም ድልን አጎናፅፈን፡፡ አላሁመ አሚን፡