Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ይህ ነው ኢስላም!

ይህ ነው ኢስላም!
የእስልምና ሃይማኖት፡- እምነትና ህግጋት ሲሆን በእምነትነቱም ይሁን በህግጋቱ የተሟላ ነው፡፡
1. በተውሒድ (አላህን በብቸኝነት ማምለክን) ሲያዝ ከሽርክ (በአላህ ላይ ሌላን አካላት ማጋራትን) ይከለከላል፡፡
2 በአላህ መንገድ ላይ አንድ መሆንን ሲያዝ መለያየትንና በቡድን መከፋፈልን ይከለክላል።
3 ወንድማማችነትን ፣ መመካከርን መተሳሰብና መተጋገዝን ሲያዝ ጥላቻን ፣ መናናቅን ፣ ሀሜትን ፣ ምቀኝነትንና ተንኮልን ይከለክላል።
4. በእውነተኝነት ሲያዝ ከውሸት ይከለክላል።
5. በፍትሃዊነት ሲያዘ ከበደል ይከለክላል።
6. ታማኝነትንና አደራ ጠባቂነትን ሲያዝ እምነት አጉዳይነትንና ማጭበርበርን ይከለክላል፡፡
7. ቃል ኪዳን አክባሪነትን ሲያዝ ቃል አባይነትን ይከለክላል።
8. ለወላጆች መልካም መዋልን ሲያዝ ወላጆችን ማመፅን ይከለክላል፡፡
9. ዝምድናን መቀጠልን ያዛል ዝምድና መቁረጥን ይከለክላል።
10. መልካም ጉርብትናን ያዛል መጥፎ ጉርብትናን ይከላከላል፡፡
በጥቅሉም እስልምና ሃይማኖት በመልካም ባህሪዎች ሁሉ ሲያዝ ከመጥፎ ባህሪዎች ደግሞ ይከለክላል፡፡
ለዚህም አላህ እንዲህ ይላል፡-
﴿ إِنَّ اللّهَ يَأْمُرُ بـِالْعَدْلِ وَالإِحْسَانِ وَإِيتَاء ذِي الْقُرْبَى وَيَنْهَى عَنِ الْفَحْشَاء وَالْمُنكَرِ وَالْبَغْيِ يَعِظُكُمْ لَعَلَّكُمْ تَذَكَّرُونَ ﴾ سورة النحل 90
“አላህ በማስተካከል፣ በማሳመርም፣ ለዝምድና ባለቤት በመስጠትም ያዛል፡፡ ከአስከፊም (ከማመንዘር)፣ ከሚጠላም ነገር ሁሉ፣ ከመበደልም ይከለክላል፡፡ ትገነዘቡ ዘንድ ይገስጻችኋል፡፡”
(አል ነህል 9ዐ)
እስልምናን ለወፈቀን አላህ የላቀ ምስጋና ይገባው!
Haider Khedir