ያልተረጋገጠ ወሬ ከማሰራጨት እንቆጠብ!
ኢስላም በእውነት ላይ አጥብቆ ያዛል፡፡ ከውሸት ደግሞ አጥብቆ ይከለክላል፡፡ ውሸትነቱ የታወቀው ይቅርና ያላረጋገጥነውን ወሬ ማውራት እራሱ አይፈቀድልንም፡፡ ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም “አንድ ሰው የሰማውን ሁሉ (ሳያጣራ) ማውራቱ ውሸታም ለመባል በቂው ነው!!” ይላሉ፡፡
የሰው ልጅ በብዛት ለእንቶ ፈንቶ ወሬ፣ እንግዳ ለሆኑ ተረቶች ተዘንባይ ነው፡፡ አስታውሳለሁ በአንድ ወቅት አንድ አስተማሪ እያስተማረ ሳለ የክፍሉ ተማሪ ከፊሉ ማንቀላፋት ያዘ፡፡ ከፊሉ ተሰላችቶ ትኩረቱን ነፍጓል፡፡ ከፊሉ ደግሞ አካሉን ብቻ ለመምህሩ ጎልቶለት በሀሳብ ጭልጥ ብሎ ሄዷል፡፡ ድንገት መምህሩ እንግዳ የሆነ ነገር ማውራት ጀመረ፡፡ “የሆነ እንስሳ ነበር፡፡ አራት አይን ያለው፣ ስምንት ቀንድ ያለው፣ እ ሶስት አፍንጫ ያለው፣…” እያለ ሲያወራ ያንቀላፋው ነቃ፡፡ የተሰላቸው ትኩረቱን ሰበሰበ፡፡ በሀሳብ የነጎደው ከመቅፀብት ተመልሶ ጆሮውን ቀሰረ፡፡ ከዚያ አስተማሪው ምን ቢለን ጥሩ ነው? “ያወራሁት ነገር እውነት አይደለም፡፡ እንዲህ አይነት እንስሳ የለም፡፡ እናንተ ግን ትገርማላችሁ፡፡ ቁም-ነገር ሳወራችሁ ተዘናግታችሁ ለውሸት ሲሆን ትነቃላችሁ” አለን፡፡ ይህን ታሪክ ያስታወሰኝ ዛሬ ያለንበት ሁኔታ ነው፡፡ ከአንድ ቁርኣናዊ ወይም ሐዲሣዊ ቁም-ነገር ይልቅ ያለ አንድ ማስረጃ እርቃናቸውን የሚተላለፉ እንቶ ፈንቶዎች እጅግ ሰፊ አራጋቢ ሲያገኙ ማየት የሚደንቅ ነው፡፡ የዛሬን ስንት አመት ጀምሮ “የነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ቀብር ጠባቂ ነኝ” በሚል ሰው የተፃፈ ተራ እንቶ ፈንቶ በስፋት እየተባዛ ሲሰራጭ ነበር፡፡ በዐረብኛ፣ በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ ... እያባዙ ሲያሰራጩ ህሊናቸው የማስረጃ ደወል እንኳን አለማቃጨሉ እጅጉን የሚደንቅ ነው፡፡ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ “እኔ በዚህ የሚሸወድ ይኖራል ብየ ስላልገመትኩ ችላ ብየው ነበር” ይላሉ፡፡ ጉዳዩ ግን ዛሬም አልተቋረጠም፡፡
በውሸት ታሪክ እምነታቸውን ለማስፋፋት ደፋ ቀና የሚሉት ከሃዲዎችና የስሜት ተከታዮች ናቸው፡፡ ለምሳሌ ጴንጤዎች ሰፈር ይሄ ነገር በስፋት የሚታወቅ ነው፡፡ “የአልቃኢዳ አባል የነበረው እንቶኔ አፍጋኒስታን ውስጥ ጌታ ተገልጦለት ክርስቲያን ሆነ” ብለው የውሸት ታሪክ ይሰራሉ፡፡ አይቆዩም ያንኑ ምስል ሀገሩን ወይም ስሙን ብቻ ቀይረው ያሳያሉ፡፡ ያለ ምንም እፍረት ሌላ ጊዜ ደግሞ ያንኑ ምስል ሶሪያ ላይ፣ ዒራቅ ላይ፣ ፍልስጤም ላይ እያሉ እያፈራረቁ ያሳያሉ፡፡
መልኩ ይለያል እንጂ ከሙስሊሞች መሀልም እንቶ ፈንቶ ወሬዎች እየሰበሰበ ለስብከት የሚጠቀም በደንብ አለ፡፡
- “ቁርኣንን ያቃጠለው እንቶኔ እንዲህ ሆነ” ብለው ምስል ያሳያሉ፡፡ ያለምንም ማስረጃ!
- “እከሌ የሚባለው ሳይንቲስት ጨረቃ ላይ ሆኖ አዛን በመስማቱ ሰለመ” ብለው ያወጣሉ፡፡
- ሌላው “በከዕባ አናት ላይ ምንም አይነት በራሪ (ወፍ፣ አውሮፕላን፣…) ማለፍ አይችልም” ብሎ ያወጣል፡፡
- ሌላው “ለይለተል ቀድር እንዳለ የናሳ ሳይንቲሰቶች አረጋገጡ” ብሎ ያወጣል፡፡
- ሌላው ሶላት የማይሰግድ ሰው አስከሬን ነው ብሎ እባብ የተጠመጠመበት አስከሬን ያሳያል፡፡ የተወሰደው ግን ማሌዢያ ውስጥ ከተሰራ ፊልም ላይ ነው፡፡
አሁን ይህን ነገር ለመፃፍ ያነሳሳኝ የዛሬን ስንት አመት “አንዷ ቁርኣንን በመወርወሯ ምክንያት ምንነቱ ወደማይታወቅ እንስሳነት ተለወጠች” እያሉ ሲያወጡት የነበረውን የውሸት ታሪክ እንዳዲስ የሚያራግቡ ሰዎች ስላየሁ ነው፡፡ ያኔ ታሪኩን የቀጠፈው አካል ማስተባበያ በማውጣት ይቅርታ ጠይቆ ነበር፡፡ በሚገርም ሁኔታ እኛም ሀገር ጋዜጣ ላይ ጭምር አውጥተውት ነበር፡፡ ዛሬ ግን ይበልጥ የሚያበሳጨው ጉዳዩ ውሸት ከመሆኑም ባለፈ ቁርኣንን ረግጦ የቆመ ሰው ምስል በጎን አቁመው ማሳየታቸው ነው፡፡ ይሄንኑ ጥፋት በየማህበራዊ ሚዲያው ያሰራጩታል፡፡ ቆይ ለምን የሙስሊሞችን ቅስም ይሰብራሉ?! ደግሞ አያፍሩም እንዲህ አይነት በውሸት የታጀበ ተራ እንቶ ፈንቶ ለጥፈው ከስር “አላሁ አክበር በሉ” እያሉ ፔጃቸውን ማስተዋወቃቸው ነው፡፡
ከፊሎቹ እነዚህ እንቶ ፈንቶዎች በሙስሊሞች ህሊና የሚሳለቁ ሴረኞች ውጤቶች ናቸው፡፡ ወይም ደግሞ ሃይማኖት ማለት በእንዲህ አይነት ተራ እንቶ ፈንቶ ተቀጣጥሎ የሚደገፍ ውሽልሽል እምነት እንደሆነ በመስበክ አንዳንዶች ጭራሽ ከሃይማኖት እንዲሸሹ ለማድረግ የታቀደ ሴራ አካል ነው፡፡
ከፊሎቹ ደግሞ ገፃቸውን በዲን ሂሳብ ማስተዋወቅ የሚሹ ብልጣ ብልጥ መሳይ ቂላቂሎች ውጤቶች ናቸው፡፡ “ሱብሓነላህ ሳትሉ እንዳታልፉ፡፡” “አላሁ አክበር በሉ”፤ “ይህን የፈፀመ እንዲህ አይነት እድል ያገኛል”፤ “ይህን ያልፈፀመ እንዲህ አይነት አደጋ ይደርስበታል”፤ ወዘተ ይላሉ፡፡ ስለዚህ ከፊሎቹ የቂላ ቂሎች ስራ ሲሆኑ ከፊሎቹ ደግሞ የሴረኞች ስራዎች ናቸው፡፡ ሳይታወቀን የማንን ስራ እየፈፀምን እንደሆነ እያስተዋልን፡፡
ሌሎችም አሉ፡፡ ጥፋታቸው እንደነዚህ ባይጋነንም የነዚህን አጠፊዎች ተንኮል ተከትለው ገፆቻቸውን በእንቶ ፈንቶ የሚያስተዋውቁ፡፡ “አሁን ይሄ አንድ ሺ ላይክ አይገባውም?” “እከሌን የምትወዱ አንድ ቁጥር ፃፉ፡፡” “እውነት ነብዩን ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም የምትወድ ከሆነ ሶላት ሳታወርድ እንዳታልፍ!”፤ “በአላህ እንትን ሳትል እንዳታልፍ” ወዘተ ይላሉ፡፡ ሌሎችም ደግሞ የሂሳብ ጥያቄ፣ እንቆቅልሽ፣… ወዘተ እየጠየቁ በእንቶ ፈንቶ ገፃቸውን የሚያስተዋውቁ አሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ “በመጀመሪያ ላይክ ያርጉ፡፡ ከዚያም 333 ይፃፉ፡፡ ከዚያም…” እያሉ ሰዎች የጥፋት ፔጃቸውን እንዲወዱላቸው ያደርጋሉ፡፡
ከነዚህ የከፋው ደግሞ ጥንቆላ ውስጥ የተሰማሩት ናቸው፡፡ የትዳር አጋር፣ የፍቅር ጓደኛ፣ የመሞቻ ጊዜ፣ የሚሞቱበትን ሰበብ፣ የስራ ድርሻ፣… ላይ በመጠንቆል ጥፋት ላይ የተሰማሩ አሉ፡፡ እነዚህ እምነትን የሚያናጉ አደገኛ ጥፋቶች ናቸው፡፡
ሲጠቃለል ያለ ማስረጃ ነገሮችን አናራግብ፡፡ የቂላቂሎች ሰለባም አንሁን፡፡ ያለበለዚያ ስለሚፈጠረው የተዛባ እምነት፣ ስለሚከሰተው የዐቂዳ ብልሽት፣ ወደ ሌሎች ስለሚደርሱት የብልግና ምስሎችና መልእክቶች… ተጠያቂ እንሆናለን፡፡ ወላሁ አዕለም፡፡
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 10/2009)