Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ረጀብን አስመልክቶ...


ረጀብን አስመልክቶ... (1)
ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ & ምርጡ ተማሪያቸው ኢብኑል ቀዪም አልጀውዚያህ ረጀብን አስመልክተው እንዲህ ብለዋል፤
قال شيخ الإسلام ابن تيمية رحمه الله:
«وأما صوم رجب بخصوصه فأحاديثه كلها ضعيفة، بل موضوعة، لا يعتمد أهل العلم على شيء منها ، وليست من الضعيف الذي يروى في الفضائل ، بل عامتها من الموضوعات المكذوبات» انتهى باختصار من
مجموع الفتاوى (25/290)

ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ:-
«ረጀብን አስመልክቶ መፆምን በተመለከተ ያሉ ሀዲሶች በሙሉ ደካማ (ደኢፍ) ናቸው። እንደውም የተፈበረኩ (መውዱዕ) ናቸው። ኡለማዎች አንዱንም ሀዲስ በመረጃነት አይጠቀሙም። ለፈዳኢልም ቢሆን የሚጠቀሱ አይነት አይደሉም። እንደዉም አብዛኛዎቹ የውሸት ዘገባዎች (መውዱዓት) ናቸው።» መጅሙዕ ፈታዋ 25/290
قال ابن القيم رحمه الله :
«كل حديث في ذكر صيام رجب وصلاة بعض الليالي فيه فهو كذب مفترى»
انتهى من "المنار المنيف" (ص96)
ኢብኑልቀይምም (ረሂምሁላህ) እንዲህ ብለዋል፤
«ረጀብን መፆምን ወይም የረጀብ አንዳንድ ለሊቶችን በሰላት ማሳለፍን የሚያትት ሀዲስ ሁሉ የተዋሸ (ዘገባ ነው)» አልመናር አልሙኒፍ ገፅ 96

__________________________________________________________
ረጀብን አስመልክቶ (2)
ልዩ የረጀብ ፆም የሚባል የለም!
«የረጀብን ትሩፋቶች አስመልክቶ ትክክለኛ ሀዲስ አልተዘገበም። ከበፊቱ ካለው የጁማደል አኺራህ ወር የሚለየው ከተከበሩት (አሽሁሩል ሁሩም) ወራት በመሆኑ ብቻ ነው። ይሁን እንጂ፤ ምንም አይነት የተደነገገ ፆም የለበትም። በልዩ መልኩ የተደነገገ ሰላትም የለበትም። ኡምራም አልተደነገገም። (ከዚህ አኳያ) እንደሌሎቹ ወራቶች ነው።» ሊቃኡል ባብ አልመፍቱህ 26/174
قال ابن عثيمين رحمه الله :
" لم يرد في فضل رجب حديثٌ صحيح ، ولا يمتاز شهر رجب عن جمادى الآخرة الذي قبله إلا بأنه من الأشهر الحرم فقط ، وإلا ليس فيه صيام مشروع، ولا صلاة مشروعة، ولا عمرة
مشروعة ولا شيء، هو كغيره من الشهور " انتهى ملخصا.
"لقاء الباب المفتوح" (174/ 26) بترقيم الشاملة
 _________________________________________________________

ረጀብን አስመልክቶ (3)
ስለ «ረጀብ» ትሩፋቶች ብዙ ሰምተው ይሆናል፤
የአሊሞችን አስተያየት ልብ ይበሉ!!
አልሀፊዝ ኢብኑ ሀጀር (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል፤
« ሰለ ረጀብ ትሩፋት፣ ረጀብን ሙሉ ሰለመፆም ወይም ከረጀብ አንድን ቀን መፆምን፤ እንዲሁም ከረጀብ አንድን ለሊት መፆምን አስመልክቶ የተላለፈ ለመረጃነት የሚበቃ ሰሂህ ሀዲስ የለም» ተብዪን አል―አጀብ ገፅ 11
قال الحافظ ابن حجر رحمه الله : " لم يرد في فضل شهر رجب، ولا في صيامه ولا صيام شيء منه معين، ولا في قيام ليلة مخصوصة فيه حديث صحيح يصلح للحجة " انتهى .
"تبيين العجب" (ص11)