Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

እርዝ

'እርዝ
ትርጉሙ፦ እርዝ ከክፋት ይጠብቅ ዘንድ ታሽጎ አንገት ላይ የሚንጠለጠል ፅሁፍ፣ ክሮች፣ አጥንቶች የመሳሰሉ ነገሮች ሲሆን ድሮ ዓረቦች በተሳሳተ አመለካከታቸው ልጆችን ከሰው አይን ለመከላከል የሚያንጠለጥሉላቸው ጥቅምን ለማግኘት ወይም ጉዳትን ለመከላከል በማሰብ የሚደረግ ነው፡፡

ሸሪዓዊ ብይኑ፦ ሀራም (የተከለከለ) ከመሆኑም በላይ ከሽርክ አይነቶች አንዱ ነው፡፡ ምክንያቱ ከአላህ ውጭ በሆነ ነገር መንጠልጠል ነው፡፡ ክፉን መካች አላህ ብቻ በመሆኑ ማንኛውም ሰው ጎጂን ነገር መከላከል ያለበት በአላህ በስሞቹና በባህሪያቱ ብቻ ነው፡፡
- ኢብኑ መስዑድ እንዳሉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ሲሉ ሰምቻለው ‹‹ሩቃ፣ እርዝና መስተፋቅር መስራት ሽርክ ነው” 
- አብደላህ ኢብኑ ዑከይም እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “በአንድ ነገር ላይ የተንጠለጠለ ወደ ለርሱ ይተዋል” 
- ዑቅበት ኢብን ዓሚር እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “እርዝን ያንጠለጠለ አላህ አይሙላለት፣ ዛጎልንም ያንጠለጠለ አላህ አይተውለት” 
- ዑቅበት ኢብን ዓሚር እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል “እርዝን ያንጠለጠለ ሽርክን ፈፅሟል” 
እነዚህና መሰል ጥቅሶች ዓረቦች በብዛት ሲያንጠለጥሉት የነበሩትን ሽርካዊ እርዞች የሚከለክሉ ሲሆኑ የተከለከሉትም ከአላህ ውጭ በሆነ ፍጡር ላይ መንጠልጠል በመሆኑ ነው፡፡

የሚንጠላጠለው ፅሑፍ የቁርአን ቃል ከሆነ፦ ዑለማዎች በዚህ ዙሪያ አልተስማሙም ከፊሉ የሚፈቅድ ሲሆን ሌላው ደግሞ ይከለክላል፡፡ ቁርአንን ለፈውስ ማንጠልጠል አይቻልም የሚሉ አቋሟቸው ከአራት ምክንያቶች አንፃር ሲታይ ትክክል ነው፡፡
1. ነብዩ እርዝን የከለከሉት በጥቅሉ ሲሆን ይህን አይነቱን ነጥሎ የሚያወጣ ማስረጃ አለመኖሩ፡፡
2. ይህን መፍቀድ ከቁርአን ያልሆነን ፅሁፍ ለማንጠልጠል መንገድ ስለሚከፍትና ወደ መጥፎ የሚመራን መንገድ መዝጋት ደግሞ ተፈላጊ ስለሆነ::
3. አንጠልጣዩ በመፀዳጃ፣ በኢስቲንጃና በመሳሰሉት ቦታ ይዞት ስለሚገኝ ቁርአንን ዝቅ የሚያደርግ በመሆኑ፡፡
4. በቁርአን መፈወስ በምን መልኩ መሆን እንዳለበት ስለተገለፀ (እሱም ህመምተኛው ላይ መቅራት ነው) እና ይህን መተላለፍ ስለማይቻል፡፡'

4. በቁርአን መፈወስ በምን መልኩ መሆን እንዳለበት ስለተገለፀ (እሱም ህመምተኛው ላይ መቅራት ነው) እና ይህን መተላለፍ ስለማይቻል፡፡

Post a Comment

0 Comments