Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

አንዳንድ ወንድሞች ባለማወቅ ወይንም በቸልተኝነት በሠላት ዙርያ ከሚሠሯቸው ስህተቶች መካከል

አንዳንድ ወንድሞች ባለማወቅ ወይንም በቸልተኝነት በሠላት ዙርያ ከሚሠሯቸው ስህተቶች
መካከል
1 ወደ መስጂድ በሚሄድበት ግዜ ሠላቱ ወይም ረከአው ላይ ለመድረስ በጣም መቻኮል.
ወይም መሮጥ ፦ ረከአው እና ሠላቱ ላይ ሊደርስ ይችላል ነገር ግን ሠላት ውስጥ ሲገባ
ማሟላቱ የግድ የሚሆነውን አርካን ይተዋል እሡም ሠኪና (እርጋታ) አይኖረውም
እንደውም እየሮጠ በመጣበት ትንፋሹ. (ህህ…ቢስሚላሂ…ህ……)ምናምን. እያለ በግራና
በቀኝ በኩል ያሉትን ሠጋጆች ይወሠውሣል ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ግን ይህን
አላዘዙም እንዲህ ነበር ያሉት ((ሠላት በተቆመች ግዜ እየሮጣችሁ እንዳትመጡ ፣
አየተራመዳችሁ ኑ በእርጋታ ላይ አደራችሁን))
~ ወደ መስጂድ ስንሔድ ረጋ ብለን!!
2.መጥፎ ሽታ ያለውን ነገር ተጠቅሞ መስጊድ መግባት ፦ ሡብሀነላህ ወላሒ አጂብ
እኮነው ¡ ሠርግ ያለበት ሠው መቼም ነጭ ሽንኩርት በልቶ አይሔድም አይደል ምክንያቱም
የሚሔደበት ቦታ ላይ የሚጠብቁት ሠዎች ፕሮቶኮላቸውን የጠበቁ ደካማ ፍጥረቶች ጋር
ነዋ! ወደ መስጂድ ሲሄድ የሚጠብቀው ማነው? ሊያንጋግር የሚሄደው ማንን ነው?? ሡፍ
እና ጨርቃ ጨርቅ የለበሠ ተራ ግለሠብን?? ላ! ወላህ ያ ኢህዋን ሀያሉን አላህ ነው
ታድያ ውዱ ጌታችንን ለማናገር ግዜ ምን ነካን?? ስለ ለበስነው! አፋችን ስላለው
አይጨነቅንም አይደል?? ሌላው ቀርቶ ሌላውን ሠላት ሠጋጅ እና መላይካዎች ለምን ከኛ
በሚወጣ አስቀያሚ ሽታ አዛ እናደርጋለን??
~ወደ ተከበረው አላህ ቤት ስንገባ ሽታ ያለው ካልሲ ፣ ነጭ ሽንኩርት ፣ ቂቤ ፣ ሢጋራ.
በአጠቃላይ መጥፎ ሽታን አስወግደን እንግባ
3 አብዘሀኛው ሠዎች ቦታ የማይሠጡት እና ዛሬ ላይ በየመስጂዱ ከፍተኛ ችግር እየሆነ
የመጣ ሞባይል ኢማሙ አላሁ አክበር ብሎ ሠላት ውስጥ ሢገባ ከ ቀኝ በኩል የ
(nokia) ከግራ (sumsng) ከመሀል ሌላ ከፊት ሌላ ከውሀላ ሌላ… አንዱ መንዙማ
አንዱ ነሺዳ ሢብስ ደሞ ዘፈን ወሊአውዙ ቢላህ መስገጃ ስፍራነቱን ትቶ የሞባይል መሸጫ
ቦታ እስኪመስል ድረስ ያንጫጩታል በጣም በጣም ደግሞ የሚገርመው.ደግሞ ሠላት
ከመጀመሩ በፊት ኢማሙ «ሞባይላችሁን» አጥፉ! እያለ ማስታወሻ መስጠቱ ነው
በየግድግዳ እና ምሦሦ ላይ የሚለጠፋትንማ ተዋቸው
~ ሠላትዎ ከሚያጠፋ ሞባይሎን ያጥፋ!!!
ሠላት ውስጥ ገባን
4 ብዙ ሠዎች.ከውጪ እየተሯሯጡ ይገቡና ኢማሙን ሩኩእ ላይ ካገኙት ያችን ረከአ
ለማግኘት ብለው ሠላታቸውን ሙሉ ለሙሉ የሚያበላሽ ተግባር ይፈፅማሉ ያለ ተክቢረተል
ኢህራም ሠላት ውስጥ ይገባሉ ሩኩን ያገኛሉ ሆኖም ሠላታቸው ግን ውድቅ ነው
~ ኢማሙን በማንኛውም ሁኔታ ላይ ብታገኘው.አንተ በተክቢረተል ኢህራም ጀምር!
5 በሠላት ውስጥ አይንን እንደ ቱሪስት አንዴ ወደላይ አንዴ ወደታች አንዴ ወደ ቀኝ አንዴ
ወደ ግራ መመልከት
~ አይንን ወደ ሡጁድ. መውረጃ ቦታ መስደድ,!!
6 እንቅስቃሴ ማብዛት ፦ አቤት የአንዳንድ ሠው ጣጣው.¡ የሚጀምረው ለሠላት አላሁ
አክበር ሢል ነው ጀርባውን ፣ ጭንቅላቱ አረ ተውት¡ በለቶት የማያውቀውን የሠውነት
ክፍሉን ያካል ፣ . እጁን ቋ… ቀጭ እያረገ ያንጫጫዋል አንዳንዱማ አጂብ እኮ እየሠገደ
ጥፍሩን ይሞሽራል ኢማሙ ረጋ ያለ ከሆነ አንዴ የመስጂዱን ፣ አንዴ እጁ ላይ ያለውን ፣
ሢያብሠው ደግሞ ከኪሡ ሞባይል አውጥቶ ሠአቱን ያያል ሡብሀን እውን እየሠገደ ነው
ወይንስ…
~ ሠላት ላይ እንቅስቃሴ አታብዛ
7 ይህ ደግሞ ከባድ አደጋ ቀድሞት ሊጨርስ ይመስል ኢማሙን መሽቀዳደም
ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም (አላህ ፊቱን ወደ አህያ ፊት ሊቀይረው ይችላል) በማለት
አስፈራርተዋል ስለዚህ ጠንቀቅ
~ ኢማሙ አላሁ አክበር ባለ ግዜ አላሁ አክበር በሉ ፝ ሩኩእ በወረደ ግዜ ሩኩእ ውረዱ …
8 በቁርአን ማንበብ ፦ የቁርአኑን መፀሀፍ ይዞ ማንበቡ ለማለት ፈልጌ ነው። ለምን ለዛሬ
ያፈዝነውን አንቀራም. ?? የማንችለውን ያስገደደን አለ እንዴ?? የለም ዛሬ ጭንቅላትህ
ላይ ያለችዋን ቅራትና አላህ ሀፊዝ.እንዲያደርግህ ለምነው ብዙ ግዜ በተራውሒ ሠላት
ላይ የሚታይ ነገር አለ ከቤት የኪስ ቁርአን ይዞ ይመጣል ከዛም ኢማሙ ፋቲሀን ጨርሶ
ሌላ ሡራ ሢጀምር ኪሡ ይገባና. ይዞ ያመጣትን ቁርአን አውጥቶ ይገልፃል ኢማሙ
ያለበትን ይፈልጋል ይፈልጋል… ሊያገኘው ካልቻለ ከጎኑ ያለው አጊንቶት የሚከታተል ከሆነ
ከሡ ያይና ይገልፀዋል ተመልከቱ እየሠገደ ነው.ከዛ እያነበበ ኢማሙን መሽቀዳደም ነው
~ ቁርአን በሚቀሬ ግዜ ዝም ብለን ማዳመጥ ነው ያለብን
9 ሩኩእ በሚወርድበት ግዜ ወደ ታች አለመዘቅዘቅ በጣምም ቀና አለማለት
~ የነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ጀርባ በሩኩእ ግዜ ቀጥ ከማለቱ የተነሣ ውሀ መሀል
ላይ ቢቀመጥ ወዴትም አይሔድም ነበር
10.በ ሡጁድ ወቅት ከሠባቱ የሠውነት ክፍል የትኛውንም ወደ ላይ ማንሣት የተከለከለ
ነው
~ በሠባት የሠውነት ክፍል ሡጁድ እንዳደሮግ ታዝዣለው
11 ወደ ዋናው ጉዳይ መጣን እውነትም ቃርያ! በጣም ያቃጥላል ስን ነገሩን ጥሎለት
የመጣውን ሠላት እቺ አመለኛ ቻይና በሠራችው አርቴፊሻል ቃሪያ ትበላሽ? አንዳንድ ፍሪኪ
ወንድሞች እነ እንትና ሡሪያቸውን እግራቸው ላይ ቲሸርታቸውን አንገታቸው ላይ ታጠቁ
ብለው ባዶ ወገባቸውን ይዘው ወደ መስጂድ ይመጣሉ ይሄ ወንድማዊ ምክር ነው
ወንድሜ እደግመዋለው ወንድሜ እነንትና አያውቁሁም አንተ ነህ ምታውቃቸው. እነሡ
አንተን አይደለም የሚሔዱበትንም የማያውቁ ቂል የአላህ ፍጥረቶች ናቸው እነሡን
መከተል ትተህ ና ወደ. ኢስላም ታሪክ .በዱንያም በአሔራ ክብርን ታገኛለህ
~ በሠላት ግዜ የሠውነት ክፍልን መሸፈን
ከሠላት ቡሀላ
12 ኡለሞች እውነት ብለዋል አንድ ቢድአ ሢመጣ አንድ ሡና ይዞ ይሔዳል በለዋል
አልተሣሣቱም ነብዩ ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም ሠላት ከተገባደደ ቡሀላ የሚባሉትን
አዝካሮች በአጠቃላይ ሢናገሩ የጀመአ ዱአዋን ረስተዋታል ማለት ነው?? ኖ ኖ ኖ… ይህማ
አይሆንም ረሡል ሠለላሁ አለይሒ ወሠለም. የተላኩትን በአጠቃላይ እንዳደረሡማ አላህን
አይደል እንዴ ያስመሠከሩት ታድያ ኬት መጣች?? ታሪኳ ብዙ ግን በአጭሩ መነሻዋና
መድረሻዋን ልንገራቹ. መነሻዋ ከአንድ ተራ ግለሠብ ኪስ ተነስታ የምደርሠው ወደ ራሡ
ኪስ ነው
~ የኛ ትዕዛዝ የሌለበትን ተግባር የፈፀመ ስራው ወደ ራሡ ተመላሽ ነው
አላህ ይበልጥ አዋቂ ነው
የአላህ ሠላትና ሠላም የነብያት መደምደሚያ በሆኑት በፋጢማ አባት ላይ ይውረድ!!