Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

"ውድ እቃ ያለቦታው እርካሽ ነው"!!! ሙስሊሟ እህቴ በሂጃብ በኒቃባችን ጠንካራ እንሁን


"ውድ እቃ ያለቦታው እርካሽ ነው"!!!

ሙስሊሟ እህቴ በሂጃብ በኒቃባችን ጠንካራ እንሁን ከላይ ለሚሰማው ከታች መሰረት ካለን አንወድቅም ማንም ሊጥለን አይችልም መጀመሪያ አኛ ጠንካራ መሆን ግድ ይለናል እሺ ሀቢቢቲ እናም እህቴ ሆይ ውዱ ሀይማኖታችን እስልምና እንዳለቀን እንዳከበረን መብትን እንዳጎናፀፈን ስለምን ዘነጋንና ነው ፋሽን የሸይጣንን መንገድ መርጠን ሪካሽ የሆነው?እራሳችንን እንጠይቅ!!

ኒቃብ ሂጃብማለት ቋንቋዊ ፍቺው መከለያ፣መጋረጃ መሸፈኛእንደማለት ነው ፡፡አማኝ የሆነች ሴት ባዕድ ሊያየው የማይገባውን የሰውነት ክፍሏን መሸፈን እንደሚገባት የሚያመላክት ቃል ነው ፡፡

#ጅልባብ ማለት ሰውነትን በሙሉ ከላይ ጀምሮ የሚሸፍን ሰፊ የሆነ የልብስ አይነት ነው። አላህ ነብዩን ለሚስቶቻቸው ለልጆቻቸው እንዲሁም ለምእመናት በሙላ ጅልባቦቻቸውን በላያቸው ላይ በመልቀቅ ፊቶቻቸውንና ደረቶቻቸውን ይሸፍኑ ዘንድ እንዲነግሩ አዟቸዋል።

አላህ(ሱ.ወ) እንዲህ ይላል፡-

يَا أَيُّهَا النَّبِيُّ قُل لِّأَزْوَاجِكَ وَبَنَاتِكَ وَنِسَاءِ لْمُؤْمِنِينَ يُدْنِينَ عَلَيْهِنَّ مِن جَلَابِيبِهِنَّ ۚ ذَٰلِكَ أَدْنَىٰ أَن يُعْرَفْنَ فَلَا يُؤْذَيْنَ ۗ وَكَانَ اللَّـهُ غَفُورًا رَّحِيمًا

አንተ ነቢዩ ሆይ! ለሚስቶቸህ፣ ለሴቶች ልጆችህም፣ ለምእምናን ሚስቶችም ከመከናነቢያዎቻቸው በላያቸው ላይ እንዲለቁ ንገራቸው፡፡ ይህ እንዲታወቁና (በባለጌዎች) እንዳይደፈሩ ለመኾን በጣም የቀረበ ነው፡፡ አላህም መሓሪ አዛኝ ነው፡፡(ሱረቱል አህዛብ ቁ.59)

ሂጃብ አላህን በማፍቀር አገልጋይ ባሪያው የሆኑ#እንስቶች የሚደርቡት የክብር ዘውድ ነው ፡፡በዚህ ዘውድ የወጣትነት ትኩስ ስሜት ይረታል፣የነፍስ ወከባ ይገታል፣ጨዋነትና ቁጥብነት ይገለፁበታል ፡፡ይህ የክብር ዘውድ ፈውስ ላጣው በሽታ መድሀኒት ፣ለተቅበጥባጭ ነፍስ ልጓም ፣ለአመፀኛ ልብ ሰንሰለት ነው።

ሂጃብ አይን አፋርነት፣ጨዋነት ፣ጥንቁቅነት የመሳሰሉ የፅድቅ ባህሪያትን ያካተተ ምጡቅ ስብዕና ነው ፡፡ማህበራዊ ትሩፋቱ የጎላ ሰማያዊ እሴት ነው ፡፡ከጨርቅ በላይ ስም ፣ከመሸፈኛ በላይ ትርጉም ያለው የእምነት ሰንደቅ ነው ፡፡በጊዜ ብዛት ማርጀት፣በስልጣኔ ምጥቀት መቀየር፣መከለስም ሆነ መሻሻል የሌለበት እንደ ማለዳ ፀሀይ ብሩህ ተስፋን የሚፈነጥቅ ዘመን የማይሽረው ፋሽን ነው ፡፡ትላንት በድንጋይ ዘመን ተለብሷል ፣ዛሬም በሳይንስና ቴክኖሎጂወቅትም እየተለበሰ እንደሆነው ሁሉ ፣በማይታወቀውነገም ሂጃብ እንደሚለበስ የሚታወቅ እውነታ ነው አሜሪካ ይሁን#አፍሪካ ፣አውሮፓ ይሁን ኤሲያ ሂጃብ ሂጃብነቱን አይለቅም ፡፡ ክረምት ብርድ ስለሆነ የሚለበስ ፣በጋ ስለሞቀ የሚወልቅ ሳይሆን ልባዊ እምነትን ዘወትር በገቢር ማሳያ ፣የኢስላማዊ ማንነት መገለጫ ነው ፡፡

ሂጃብ ተግባሩም እንደ ስሙ ነው ፡፡ከተለያዩ የማህበራዊ ህይወት ፈተናዎች በተለይም ከፆታዊ ትንኮሳ የሚጠብቅ ጋሻ ነው ፡፡በእስልምና ሴት ልጅ ሰውን ሰው አድርጎ በመልካም ኢስላማዊ ስነ-ምግባሮች የሚታነፅበት ማዕከል ነች ፡፡የዚህ የፅድቅ እና ወርቃማ እሴቶችጅርት የሚፈስበት መዐከል አጥሩ ሂጃብ ነው ፡፡ኢስላምን ማጥቃት የሚፈልጉ አካላትም ቀድመው ሂጃብ ላይ የሚዘምቱት ለዚሁ ነው ፡፡ የሙስሊሞች ጥንካሬና ስኬት የሚወሰነው በእንስቷ ነው ፡፡ ለዛም ነው የሂጃብ ካባን ደርቦ የኢስላም ዲፕሎማትናአምባሳደር ፣ ሰንደቁን አውለብላቢክዋክብት አድርጎ የሾማት ፡፡

ሂጃብ ሙስሊም ነኝ ላሉ ሁሉ ክብርና ኩራትን የሚቸር የእስልምና የምልክት ቋንቋ ነው ፡፡በፍቅር እና በሀሴት እንባ የሚለበስ ትምህርት ፣ ስራ፣ ገንዘብ ፣ ህይወት መስዕዋት የተደረገለት እና የሚደረግለት ብቸኛው ጌጥ ነው ፡፡ ሂጃብ ስጋን የሚሸፍን ነገር ግን መንፈስን የሚያፋፋ፣የሚያጎለብትና የማይነጥፍ ሀይልና ጉልበት የሚሰጠው ፣ሲቆሽሸ የሚያፀዳው ፣ሲዝግ የሚያነፃው የመንፈስ ምግብ ነው ፡፡የልብን ወደጌታዋ መንጠልጠል የሚያቃና ድልድይ ነው ፡፡

እናም እህቴ ሆይ በሂጃብ በኒቃብ ውድ እንደሆን ስለምን የሸይጣንን ፋሽን ተከትለን እራሳችንን እናርክሳለን ባረከላሁ ፊኩም