Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

በዲን ስም የሚንቀሳቀሱ ፖለቲከኞችን ተጠንቀቅ!!!

በዲን ስም የሚንቀሳቀሱ ፖለቲከኞችን ተጠንቀቅ!!!
መርሃ ግብር እያለ ከቁርአን ከሀዲስ ከሰለፉነ ሷሊሁን የሌለን አካሄድ ስሜቱን በማምለክና፣ ስሜቱን በመከተል የሚደነግግልህን፣ የራሱ ደህንነት በጣም አሳስቦት አንተን/አንቺን ለመከራ የሚዳርግህን ድብቁን በዲን ስም የሚንቀሳቀስ ፖለቲከኛ ራቀው፣ ተጠንቀቀው፣ አስጠንቅቀው።
እኛ በዚህ ዘመን ያለን ሰዎች ለፈተና የመጀመርያዎቹ አይደለንም። ከእኛ በፊት የነበሩ ደጋጎች በዲናቸው ሲፈተኑ የወሰዱት መፍትሄ ምን እንደነበር የሀይማኖታችንን መዛግብቶች እንፈትሽ፣ ያንንም መፍትሄ እንተግብር። ከዛ ውጭ ስሜትንና ቢድአን በመከተል ዲን አይረዳም።
ከነዚሁ ፖለቲከኞች ውስጥ "አህባሽን ለፖለቲካው አጀንዳ ብቻ ነው የምንቃወመው።" የሚልም ሙስሊሞች የሚያታል አለ።
ይሀው ፖለቲከኛና ቁማርተኛ የአህባሽ የጡት አባት የሆነውን "አሽዐሪ/ሱፍያ" ሀቅ ላይ እንደሆኑና፣ አህባሽን በመንካት ስም "አሽዐሪ/ሱፍያን" መንካት ታላቅ ስህተት እንደሆነ ከዚህ በፊት ደስኩሯል።
ሙስሉሞች ሆይ! እነዚህ ቁማርተኛ ፖለቲከኞች የነሱን ጥመት ያልተቀበለን ሁሉ "የመንግስት ደጋፊ፣ ሙናፊቅ" እያሉ ሲያከፍሩ በሌላ ጎን የነሱን የፖለቲካ አካሄድ የሚደግፉላቸውን በአላህና በመልክተኛው የማያምኑ ካፊሮችን "ክርስትያን ወንድሞቻችን" ሲሉ በገዛ አንደበታቸው ጥመት ላይ መሆናቸውን ይፋ አድርገዋል።
አማኞች ላይ ሲበረቱ ለካፊር ፖለቲከኞች ለስላሳ ናቸው እነዚህ በኢስላም ስም የሚነግዱ ፖለቲከኞች።
አገራችን ላይ ሽርክና ቢድአ ላይ የወደቀው አህባሽ ብቻ ነው እንዴ?????
በፍፁም
ሱፍያ/አሽአርያ፣ ቲጃንያና ሌሎችም የጥመት ጭፍራዎች ሽርክና ቢድአ አለባቸው።
ታድያ ህዝባችንን በመርሀ ግብር ስም ፖለቲከኛ ያደረገው ይህ ቁማርተኛ አካል ለምን የነ ሱፍያ አሽአርያን ሽርክ፣ ኩፍር፣ ቢድዐ ዝም ማለትና ማድበስበስ አስፈለገው እውነት ለኢስላም ከሆነ ከተደበቀበት ቦታ ሆኖ የሚሰራው???
ሙስሊም ወንድምና እህቶቼ በዲን ስም የሚደረግ ሁሉ ዲን አይደለም ከሸሪአ ማስረጃ እስካልደገፈው ድረስ።
እነዚህን ፖለቲከኞች፣ ቁማርተኞች ተጠንቀቋቸው፣ ከነሱም አስጠንቅቁ። ይህን ቂላቂል ትእዛዛቸውን እፈፅማለሁ ብላችሁ እራሳችሁን ማስረጃ ለሌለው ተግባር መከራ ውስጥ አትጣሉ።
አላህ ሆይ! በዲን ስም ከሚነግዱ አለም ላይ ካሉ አታላዮች አንተው ጠብቀን።