Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ይሄ ጉዳይ ወቅታዊ አይደለም ለምትሉ

ይሄ ጉዳይ ወቅታዊ አይደለም ለምትሉ
********************************
1☞. ሰይድ ቁጥብ ስለተነካ “አይሁድ ናችሁ፣
በጀርባችሁ ምን አለ…” ወዘተ ለምትወዝቱ በራሳችሁ
ሂሳብ መሰረት አብደላህ አልሀረሪንም ስትነኩ እንዲሁ
ትባላላችሁ፡፡ ምክኒያቱም በርካታ የጋራ ጥመት
አላቸውና፡፡
2☞. ሰይድ ቁጥብ ኡማውን አላከፈረም ብላችሁ
እያወቃችሁ ለምታጭበረብሩ አላዋቂ እስከሚነቃ ድረስ
እድሜ ማራዘሚያ መስሏችሁ ይሆናል ቀርዷዊ እራሱ
መስክሯል፡፡
3☞. እንዳውም የናንተው ሰይድ ቁጥብ ሶሃባ
በመሳደብ አብደላህ አልሀረሪን በደንብ ይበልጠዋል፡፡
4.☞ ይህን ስትባሉ “አህባሽ ናችሁ” ለምትሉ፣ ሶሃባ
የሚሳደብን፣ ሙስሊም የሚያከፍርን፣ … ሰው ማጋለጥ
አህባሽ ካስባለ አብደላህ አልሀረሪን ማጋለጥም
እንዲሁ ያስብላል፡፡ አሁን ይሄ ከባድ ሂሳብ ነው?!
5.☞ አንዴ አይሑድ ናችሁ፣ ሌላ ጊዜ ጴንጤ ናችሁ፣
ወዘተ ለምትሉ አሁንም እጠብቃችሁላሁ፤ አንድ ነገር
ያዙ:: እውነት ተክፊሩ ማነው? እኛ ወይሥ እናንተ? አይ
የሰይድ ቁጥብን ተክፊርነት የተናገረ ተክፊር ነው
የምትሉ ከሆነ የአህባሹንም የሚናገር እንዲሁ ተክፊር
ነው፡፡
6☞. ምናልባት አንዳንድ የሰይድ ቁጥብ አድናቂዎች
የሚሸፋፍኗቸው የመሪያቸው ጥፋቶች ሰው ጋር ሲደርሱ
የሚፈጥሩትን በመስጋት መልስ ሲያጡ ጭራሹ
እየዋሻችሁበት ነው ብለው ሽምጥጥ ያደርጋሉ፡፡ እድሜ
ማራዘሚያ ሊሆናችሁ ይችላል፡፡ በጭፍኑ
የሚከተሏችሁን ለጊዜው ትሸውዳላችሁ፡፡ ግን ለጊዜው
ነው፡፡
7.☞ የሞተ ሰው አትንኩ፤ ከፈለገ አላህ ይጠይቃቸው፣
እናንተ ምን አገባችሁ፣… ለምትሉ ካልሰማችሁ
አብደላህ አልሀረሪም ሞቷል፡፡ ሶሃባ ሲሳደብ ዝም
እንበለው? ኡማውን ሲያከፍር ዝም እንበለው? ምንኛ
የሚያስጠላ ሂሳብ ነው የምትሰሩት?!
8☞. “ይሄ ወቅታዊ ጉዳይ አይደለም አይደለም”
ለምትሉ እኔም እላለሁ እንግዲያውስ የአህባሽም
ጉዳይ ወቅታዊ ጉዳይ አይደለም፡፡ ጥፋታቸው የጋራ
ጥፋት ነው፡፡ አህባሽ ምን አመጣብን? ሶሃባ መሳደብ
አይደለምን? ሙስሊሙን ማክፈር አይደለምን?
የአላህን ከአርሽ በላይ መሆን ማስተባበል አይደለምን?
እውነት የምንቃወመው ለዲን ተቆርቁረን ከሆነ እነኚህ
ጥፋቶች ሰይድ ቁጥብም ጋር አሉ፡፡ እሱ ጋር የሌሉ ግን
አህባሽ ጋር ያሉ ጥፋቶችን ብትቆጥሩ፣ አህባሽ ጋር
የሌሉ እሱ ጋር ያሉ ጥፋቶችም አሉ

Post a Comment

0 Comments