Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ከቀዷ ፆምና ከሸዋል ፆም የትኛው ይቀደማል?




ከቀዷ ፆምና ከሸዋል ፆም የትኛው ይቀደማል?
በተለያዩ ምክኒያቶች ረመዳንን አሟልቶ ያልፆመና ቀዷ ያለበት ሰው፤ የስድስቱን ቀናት የሸዋል ፆም ያስቀድማል ወይስ በቅድሚያ ያለበትን ቀዷ በመክፈል የረመዳንን ፆም ያሟላል?
عَنْ أَبِي أَيُّوبَ الْأَنْصَارِيِّ رَضِيَ اللَّهُ عَنْهُ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ : ( مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ كَانَ كَصِيَامِ الدَّهْرِ ) رواه مسلم في صحيحه
አል ኢማም ሙስሊም ከአቡ አዩብ አልአንሳሪይ በተረጋገጠ ሰነድ ባሰፈሩት ሀዲስ የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል፤ «የረመዳንን ፆም የፆመ፤ ከዚያም ከሸዋል ወር የስድስት ቀናትን (ፆም) ያስከተለ፤ አንድ አመት እንደመፆመ ሰው ነው።»
በዚህ ሀዲስ ላይ "ثم" [ከዚያም] የሚለው ቃል ቅደም ተከተልንና አንድን ነገር ተከትሎ መምጣትን የሚያመላክት ነው። ስለዚህም ይህንን ታላቅ ምንዳ እንደሚያገኝ ቃል የተገባለት፤ ረመዳንን አሟልቶ ከፆመና ግዴታውን ከተወጣ ያለበትንም ቀዷእ ከከፈለ በኋላ ከሸዋል ወር የስድስት ቀናትን ፆም ያስከተለ ሰው ብቻ ነው። ምክኒያቱም ቀዷእ ያለበት ሰው ከረመዳን ከፊሉን ፆሟል እንጂ ረመዳንን ፆሟል አይባልም።
ታለቁ የፊቅህ ሊቅ ሸይኽ ሙሀመድ ቢን ሷሊህ አል–ኡሰይሚን (ረሂመሁላህ) እንዲህ ብለዋል¹
«የስድስቱን የሸዋል ቀናት ፆም በተመለከተ፤ ከረመዳን ጋር የተያያዙ ናቸውና የምንፆማቸው የረመዳንን ቀዷ በማውጣት ከከፈልን በኃላ ነው። አንድ ሰው የረመዳንን ቀዷ ሳያወጣ በፊት የሸዋልን ቀናት ከፆመ ለስድስቱ የሸዋል ቀናት ጿሚዎች የተገባውን ምንዳ አያገኝም። ይህም በተከታዩ የመልእክተኛው ሀዲስ መሰረት ነው። {የረመዳንን ፆም የፆመ፤ ከዚያም ከሸዋል ወር የስድስት ቀናትን (ፆም) ያስከተለ አንድ አመት እንደመፆመ ነው}
እንደሚታወቀው፤ አንድ ሰው ረመዳንን ፆሟል የሚባለው ያለበትን ቀዷ አሟልቶ ሲከፍል ነው። አንዳንድ ሰዎች የሸዋል ፆም እንዳያመልጣቸው በመስጋት ያለባቸውን ቀዷ ባይከፍሉም የስድስቱን የሸዋል ቀናት ይፆማሉ። ይህ ደግሞ ከባድ ስህተት ነው። [የተጠቀሰውን ምንዳ ለማግዘነት] አንድ ሰው እነዚህን ቀናት ሊፆም የሚገባው ያለበትን የረመዳን ቀዷ ከከፈለ በኀላ ነው።» መጅሙኡል ፈታዋ 20/438
ይህ በሀዲሱ የተጠቀሰውን ታላቅ ምንዳ ከማግኘት አንፃር እንጂ የረመዳንን ቀዷ ማቆየትና ቀጣዩ ረመዳን ከመምጣቱ በፊት ቀዳውን መክፈል የተፈቀደ ነው። ምንም እንኳ በዚህ ሀዲስ ላይ የተጠቀሰውን አጅር ባያገኝም
አንድ ሰው በሸዋል ወር የረመዳንን ቀዷ ሳይከፍል በፊት እንደ ሰኞና ሀሙስ፣ ወይም አያመልቢድ ያሉ ፆሞችን መፆም ይፈቀድለታል።
والحمد لله رب العالمين
أبو جنيد
شوال 1436/1 هے
--------------------------
¹ قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله رحمة واسعة «أما صيام ستة أيام من شوال فإنها مرتبطة برمضان ولا تكون إلا بعد قضائه ، فلو صامها قبل القضاء لم يحصل على أجرها ، لقول النبي صلى الله عليه وسلم : « من صام رمضان ثم أتبعه بست من شوال فكأنما صام الدهر » ومعلوم أن من عليه قضاء فإنه لا يعد صائما رمضان حتى يكمل القضاء ، وهذه مسألة يظن بعض الناس أنه إذا خاف خروج شوال قبل صوم الست فإنه يصومها ولو بقي عليه القضاء ، وهذا غلط فإن هذه الستة لا تصام إلا إذا أكمل الإنسان ما عليه من رمضان " مجموع فتاوى ابن عثيمين (20/438)

Abujunaid Salah Ahmed