Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ጥያቄ፦ ቀዷ ያለበት ሰው ስድስቱን ሸዋል ቢፆም እንዴትይታያል? (ሸይኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል ዑሰይሚን ረሒመሁላህ)



ጥያቄ፦ ቀዷ ያለበት ሰው ስድስቱን ሸዋል ቢፆም እንዴትይታያል?

መልስ፦ ለዚህ የምንሰጠው መልስ ከነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) ቃል ነው። ነቢዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) << ረመዳንን የፆመ ከዚያም እሱን አስከትሎ ከሻዋል ስድስት ቀን የፆመ ሰው አመቱን ሙሉ እንደፆመ ይቆጠራል >> ነው ያሉት (ሙስሊም )። ሰውየው የረመዳን ቀዷ እያለበት ከሸዋል ስድስቱን ቀን ከፆመ የፆመው ከረመዳን በፊት ነው ወይስ በኋላ? 
ለምሳሌ፦ ሰውየው ከረመዳን ሃያ አራት ቀን ብቻ ፆመ እንበል። ስድስት ቀን ቀዷ አለበት። የስድስቱን ቀን ቀዷ ከማውጣቱ በፊት ስድስቱን የሸዋል ፆም ቢፆም ረመዳንን ፆሞ ስድስቱን የሸዋል ፆም አስከተለ አይባልም። ምክንያቱም የረመዳንን ጾም እሰካላሟላ ድረስ ረመዳንን ፆሟል አይባልም። ስለዚህ የረመዳንን ፆም ቀዷ እያለበት ስድስቱን የሸዋል ፆም የፆመ ሰው ስድስቱ የሸዋል ፆም አጅር አይፀናለትም።
ይህ ጉዳይ ሰውየው የፆመ ቀዷ እያለበት ሱና መፆም ይችላል ወይስ አይችልም በሚል ዑለሞች ልዩነትን ካሳዩበት ነጥብ ጋር አንድ አይደለም። እነሱ ልዩነት (ኺላፍ) ያሳዩት ከስድስቱ የሸዋል ፆሜ ውጭ ባለው የሱና ፆም ነው። ስድስቱ የሸዋል ፆም ግን ረመዳንን የሚከተል ነው። ስለዚህ መጀመሪያ ረመዳንን ካሟላ በኋላ ለፆመ ሰው እንጂ አጅሩ ሊፀና አይችልም።
(ሸይኽ መሐመድ ኢብኑ ሷሊህ አል ዑሰይሚን ረሒመሁላህ)


Taju Nasir