Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

ለBREAK‬ (ዕረፍት) ወደ ቤተሰቦቻቹ የመጣቹ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች



ለBREAK‬ (ዕረፍት) ወደ ቤተሰቦቻቹ የመጣቹ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ቤተሰቦቻቹን በመልካም ማዘዝ በመጥፎ መከልከል በናንተ ላይ ይበልጥ የተገባ ነው ። በዩኒቨርሲቲ ቆይታቹ ከቁርኣን ጀምሮ እስከ ትላልቅ ኩቱቦች በኡስታዞቻቹ (አላህ ኸይር ጀዛቸውን ይክፈላቸው) የተማራቹት በቅድሚያ ነፍሳቹን ቀጥሎም ቤተሰቦቻቹን ብሎም የ አካባቢያቹን ሙስሊም ሕብረተሰብ ከእሳት ለማዳን ዋነኛው ምክንያት ነው።
{{ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا قُوا أَنفُسَكُمْ وَأَهْلِيكُمْ نَارًا }}
(( እናንተ ያመናችሁ ሆይ፦ ነፍሶቻችሁንና ቤተሰቦቻችሁን ከእሳት ጠብቁ)) [ተሕሪም-6]
እንደሚታወቀው ዩኒቨርሲቲ ማለት ከየክልሉ የተወጣጡ ተማሪዎች መሰባሰቢያ ተቋም ነው ። ሃገራችን ላይ በአራቱም አቅጣጫ ሽርክ ይሰራል ፣ ቢድዐ ይተገበራል ። ከሱም ብሶ ሙስሊሙ ሕዝብ በዱኒያዊ ጥቅማ ጥቅም ተደልሎ ሐይማኖቱን የሚቀይርም እንዳለ ዕሙን ነው ። ይህን ማሕበረሰብ ከማንም በፊት ሊደርስለት የሚገባው ደግሞ ከራሱ ከሕብረተሰቡ ጉያ የወጣው ፣ የተወለደበትና ያደገበትን አካባቢ ባሕል ፣ ተለምዶ ጠንቀቆ የሚያውቀው ወጣቱ ክፍል ነው ። ከዚህ ወጣት ክፍል ደግሞ የሁለተኛ ደረጃ ትምሕርቱን አጠናቆ ወደተለያዩ የሃገሪቱ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ለትምሕርት የሚሄደው ታዳጊ ትውልድ አንዱ ነው ።
ስለዚህም የያዝነውን ዓመት መንፈቅ ጨርሳቹ ለዕረፍት ወደ የቤተሰቦቻቹ የምትሄዱ ተማሪዎች በየቤታቹ ውስጥና በየአካባቢያቹ የሚገኘውን ሽርክ ፣ ቢድዓ ፣ ወንጀል ‪#‎በሒክማ‬ ለቤተሰቦቻቹ አባላት በማስተማር በቅድሚያ ከምንም በፊት ተውሒዳቸውን እንዲጠብቁ ፣ ሰላትን እንዲሰግዱ ፣ ዘካን እንዲያወጡ ፣ ረመዳንን እንዲፆሙ ፣ አቅሙ ካላቸው ሐጅ እንዲያደርጉ ፣ የጎረቤቶቻቸውን ሐቅ እንዲጠብቁ በማስተማር ወደ ጀነት ጥሪ ማድረግ ይኖርባቿል ።
وَأْمُرْ أَهْلَكَ بِالصَّلَاةِ وَاصْطَبِرْ عَلَيْهَا }}ا }}
((ቤተሰብህንም በስግደት እዘዝ፤ በርሷም ላይ ዘውትር)) [ጠሃ-132]
ወደኸይር መጣራታችን ከመጥፎም መከልከላችን ለዚህ ዑማ በላጭነት ዋናው ምልክት ነውና !!!
كُنتُمْ خَيْرَ أُمَّةٍ أُخْرِجَتْ لِلنَّاسِ تَأْمُرُونَ بِالْمَعْرُوفِ وَتَنْهَوْنَ عَنِ الْمُنكَرِ وَتُؤْمِنُونَ بِاللَّـهِ ۗ وَلَوْ آمَنَ أَهْلُ الْكِتَابِ لَكَانَ خَيْرًا لَّهُم ۚ مِّنْهُمُ الْمُؤْمِنُونَ وَأَكْثَرُهُمُ الْفَاسِقُونَ
((ለሰዎች ከተገለጸች ሕዝብ ሁሉ በላጭ ሆናችሁ፤ በጽድቅ ነገር ታዛላችሁ ከመጥፎም ነገር ትከለክላላችሁ በአላህም (አንድነት(በተውሒድ)) ታምናላችሁ፤ የመፅሐፉም ሰዎች ባመኑ ኖሮ ለነርሱ የተሻለ በሆነ ነበር፤ ከነርሱ አማኞች አሉ፤ አብዛኞቻቸዉ ግን አመፀኞች ናቸው።)) [ዒምራን-110]
ባረከላሁ ፊኩም
AS