Header Ads Widget

Ticker

6/recent/ticker-posts

የሸኽ” ሁሴን ጅብሪል ትንቢት ?????????

ዛሬ እዚው ፌስቡክ ላይ ባየሁት ነገር በጣም አዝኛለው። አንዲት ልጅ አላህ ቅኑን መንገድ ይምራት አፍሪካ ቲቪ እያየች እንደነበርና ቻናሉም ላይ የሚታዩ ሰዎችን ስም ጠርታ በጣም ካሞገሰች በህዋላና ማሳረጊያዋን ያደረገችው አንድን የሽርክ መፅሃፍ በማስተዋወቅ ነበር ።
መፅሃፉም ....
« “ » የሚለውን ሲሆን ልጅቱ የመፅሃፉን ሽፋን ከፅሁፏ ጋር አያይዛ ለጥፋ ነበር ። በመሰረቱ ልጅቱ እያሞገሰች ማንነታውን ሰቅላ የፃፈችላቸው ሰዎችን ከመፅሃፉ ጋር አያይዛ ለምን እንደለጠፈች ባይገባኝም አንድ ነገር ግን ተረድቻለው ። ይህም እነዚህ ስማቸውን ጠቅሳ እያሞገሰችና “በዚህ ሰዐት ከነርሱ ጋር መሆን ተመኘው ... ” ብላ የፃፈችላቸው ሰዎች የተፈጠረችበት ዓላማ የሆነውን ተውሒድን ዕውቀት በቲቪ ሲቀርቡ እንደማያስተምሯት (በተጨባጭም የምናየው ነው) ብሎም ይህን የሽርክ መፅሃፍ ከስማቸው ጋር ጠቅሳ መፃፏ እንዳልቆረቆራት ነው። እውነት እናውራ ከተባለ እስኪ በተውሒድና በሱና ትምሕርቱ (በቻናል አላልኩም) የምናውቀውን ወንድም ስሙን አንስታ “ይህ ሰው የሚሰጣቸው ትምሕርቶች ጠቃሚና ፍሬን ያዘሉ ናቸው ” ካለች ብህዋላ “... የሸኽ ሁሴን ጅብሪል ትንቢት ዛሬ ላይ በገሃድ እየታየና እየተከሰተ የሚገኝ ነው” ብላ ትፅፋለች ብላቹ ታስባላቹን? እኔ በጭራሽ! ነው መልሴ ። ግን ልጅቱ በእውነትም እንደዛ ብላለች ። ለፅሁፏ መደገፊያ ያደረገችው የትንቢቱን “ዕውን” መሆን ነው ።
ኢናሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን
ተውሒድን ያልተማረና ያልተረዳ ሰው ብዙ አስደንጋጭና አስፈሪ ነገሮችን ሊያወራም ሊተገብርም ይችላል ሆኖም ግን ችግሩ እሱ ሳይሆን ተውሒድን ለመረዳት አለመሞከሩና “ተረዳ” ሲባል “አሻፈረኝ” ማለቱ ነው ። ከሱም ብሶ የተመከረውን ምክር ልክ እንደ አፍራሽ ሃሳብ በአይነ ቁራኛ መመልከቱ ለውድቀቱ ሁነኛ መንስዔ ነው ።
ለማንኛውም የዚህችን ልጅ ተመኩሪ አንስቼ እንድፅፍ ያስገደደኝ በሷ ቦታ ያሉ በርካታ ወንድሞችና እሕቶች ስላሉ እነሱም ቆም ብለው ያስቡበት በሚል ስሜት ነው ።
“ሸኽ” ኑርሁሴን ጅብሪል ትንቢት የሚባለው መፅሃፍ በአብዛኛው ያዘለው ሽርክንና ኹራፋትን ነው ።
እንደሚታወቀው ነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) የነገን አውቃለሁ
ስለሚል ሰው የሚከተለውን ተናግረዋል፡፡
የነገን የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው፡፡ ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ
ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹የነገን እውቃለሁ ባይ ዘንድ የሄደ እና እሱን
የጠየቀ የ40 ሌሊት ሰላቱን አይቀበለውም፡፡›› ሙስሊም ዘግበውታል
ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ ‹‹የነገን እውቃለሁ ባይ
ዘንድ የሄደ እና እሱን የጠየቀ የ40 ለሊት ሰላቱን አይቀበለውም፡፡››
አልባኒ ሰሂህ አ-ተርጊብ ወተርሂብ
አቡ ሑረይሪ እንደተላለፈው ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ወደ
ጠንቋይ በመሄድ የሚለው የተቀበለ ሙሐመድ ላይ በወረደው ክዷል››
አቡ ዳውድ አህመድና ሃኪም
ሸህ ሁሴን ጂብሪል አሉ ተብሎ ከተፃፈው ውስጥ ስለ አፂ ቲዎድሮስ
የሚከተለውን ብለዋል ይላል
‹‹ነፍስህ ለጀነት ትሆናለች
የዕድሜህ ቁጤት ሰልስላለች›› ገፅ 47 አራት ዐይናዎቹ፡፡
እስቲ ይህ አካውንትም ሆነ ሌሎች ሽርክን ለማስፋፋት የሸህ ሁሴን
ትንቢት እያሉ የሚናገሩ ሰዎች የሚከተለውን መልስ ይስጡ
1) አፂ ቴዎድሮስ ካፊር ነው፤ ካፊርን ደግሞ ‹‹ነፍስህ ለጀነት
ትሆናለች›› ማለት ይቻላል ወይ???
2) ሸህ ሁሴን ጂንሪል ‹‹ጠጅ ይጠጣ እንደነበር›› የሚናገሩም
ሞልተዋል፡፡ የአላህ ወልዬች አላህን ያምፁት ነበር ወይ???
አላሁ ሱብሃነሁ ወተዓላ ስለ ገይብ (የነገ፤ የሪቅ ሚስጥር) አስመልክቶ
የሚከተሉትን ይላል
የሩቅን ምስጢር አውቃለሁ ባይነትና ከዚህ ጋር የተያያዙ ነጥቦች
የሩቅ ምስጢር “ገይብ” ማለት ከሰዎች አዕምሮና እይታ የተሰወረ ነገር
ሲሆን አሁን ያለ፣ ያለፈ ወይም የወደፊት ነገር ሊሆን ይችላል፡፡
ይህ የአላህ መለያ በመሆኑ ከሱሌላ ማንም ሊያውቀው አይችልም
አላህ እንዲህ ይላል፦
«በሰማያትና በምድር ያለው ሁሉ ሩቅን ምስጢር አያውቅም፡፡ ግን
አላህ (ያውቀዋል)፡፡›› (አል ነምል 65)
አስሃበል ካህፍ ስንት ዘመን እንደቆዩ የሚያውቀው አላህ ብቻ ነው፡፡
የአላህ ውድ ባሪያ ነብዩ ሙሃመድ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንኳን
አላወቁም አላህም ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይላል
«አላህ የቆዩትን ልክ ዐዋቂ ነው» በላቸው፡፡ (አል ከህፍ 26)
አላህ በመቀጠል እንዲህ ይላል
‹‹ሩቁንና ቅርቡን ዐዋቂ ታላቅ የላቀ ነው፡፡›› (ረዕድ 9)
የሩቅ ምስጢርን ከአላህ በቀር ሌላው ይቅርና የቅርብ መልአክም ሆነ
የተላከ ነብይ የሚያውቅ የለም፡፡ አላህ ስለ ኑህ ሲናገር እንዲህ
ይላል፦
ኑህ (አለይሂ ሰላም) የማያውቁትን ሸህ ሁሴን ያውቃሉ ማለት ዘበት
ነው
«ለእናንተም እኔ ዘንድ የአላህ ግምጃ ቤቶች አልሉ ሩቅንም ዐውቃለሁ
አልላችሁም (አላቸው)፡፡ ›› (አል ሁድ 31)
ስለ ሁድ ሲናገርም እንዲህ ይላል፦
«ዕውቀቱ አላህ ዘንድ ብቻ ነው፡፡ ያን በእርሱ የተላክሁበትንም
አደርስላችኋለሁ›› አላቸው፡፡ (አል አህቃፍ 23)
አላህ ለነብዩ ሙሐመድም (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ብሏል፦
«ለእናንተ የአላህ ግምጃ ቤቶች እኔ ዘንድ ናቸው አልልም፡፡ ሩቅንም
አላውቅም፡፡›› በላቸው፡፡ (አል አንዓም 5ዐ)
እንግዲህ የአላህ ውድ፤ የነብያት እና የሩሱሎች ኢማም፤ የአደም ልጅ
ምርጥ የሩቅን ካላወቁ ከሳቸው ውጭ ያሉት ጠንቋዬች እንዴት
ያውቃሉ?????
ይሀው እዚህ ጋር ደግሞ መላእክቶች እንኳን የሩቅን አያውቁም
‹‹አደምንም ስሞችን ሁሏንም አስተማረው፡፡ ከዚያም በመላእክት ላይ
(ተጠሪዎቹን) አቀረባቸው፡፡ «እውነተኞችም እንደኾናችሁ የነዚህን
(ተጠሪዎች) ስሞች ንገሩኝ» «ጥራት ይገባህ፤ ከአስተማርከን ነገር
በስተቀር ለኛ ዕውቀት የለንም፡፡ አንተ ዐዋቂው ጥበበኛው አንተ ብቻ
ነህና» (አሉ)፡፡ (አል በቀራህ 31-32)
ይህ ሆኖ ግን አላህ ለተወሰኑ ፍጡሮች ከስውር ዕውቀቶች የተወሰነ
በራዕይ ሊያሳውቂቸው ይችላል፡፡ ለምሳሌ አላህ እንዲህ ብሏል፦
«(እርሱ) ሩቁን ምስጢር ዐዋቂ ነው፡፡ በምስጢሩም ላይ አንድንም
አያሳውቅም፡፡ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ (ለሌላ
አይገልጽም)፡፡ እርሱም ከስተፊቱም ከስተኋላውም ጠባቂዎችን
ያደርግለታል፡፡ እነርሱ ዘንድ ባለው ነገር ዕውቀቱ የከበበና ነገሩንም
ሁሉ በቁጥር ያጠቃለለ ሲኾን የጌታቸውን መልክቶች ያደረሱ
መኾናቸውን ያውቅ ዘንድ (ጠባቂ ያደርጋል)፡፡›› (አል ጂን 26-28)
አላህ በዚህ አንቀፅ ላይ በግልፅ እንዳስቀመጠው፤ ገይብን አላህ
ለማንም አያሳውቅም፤ ከመልክተኞቹ ለወደደው ቢሆን እንጂ፡፡
ከነብያችን (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) በኋላ ነብይ የለም፡፡ ሸህ ሁሴን
ጂብሪል የሚባሉት ከየት ያመጡትን ነው የሚናገሩት??????
በመሆኑም እያንዳንዱ ሙስሊም የሩቅ ምስጢር አውቃለው በማለት
በሀሰት በማጭበርበር እራሳቸው ጠመው ሌላውን የሚያጠሙ
ድግምተኞችንና ኮከብ ቆጣሪ የመሳሰሉ ዋሾዎችን ሊጠነቀቅ ይገባል::
በሲኒም ያስጠንቁል፤ ጠንቋይ ቤት ይሄድ፤ የትንቢት መፀሃፍ እያለም
ያንብብ፤ ጋዜጣ ላይ ኮከብ ያስነብብ፤ በአላህ ላይ እያጋራ ነው በአላህ
ላይ ያጋራ ደግሞ
ሰላት ፆም እና የመሳሰለው እነዚህን ሰዎች ይጠቅማልን???
ሽርክ ከተደባለቀ ሰውየው እድሜ ልኩን የሰራው ስራ ውድቅ ይሆናል
አላህ ነብያቱን አስመልክቶ ስለ 18 ነብያት ገድል ከተናገረ በኋላ
‹‹ቢያጋሩ ኖሮ የሰሩት ሁሉ በታበሰ (ውድቅ) በሆነ ነበር›› ይላል፡፡
ታድያ ምነው የሽርክ ጉዳይ ተቀዳሚነት አልሰጠው አለ???
አላህ ከጠንቋዬች እና ሰራዊታቸው ተንኮል ኡማውን ይጠብቀው፡፡
የአላህ ሰላት እና ሰላም በነብያችን፤ በቤተሰቦቻቸው፤ በባልደረቦቻችን
እና ሃቅን በተከተለ ላይ ሁሉ ይሁን፡፡

Post a Comment

0 Comments